Friday, January 24, 2014

በዱባይ ማራቶን በወንዶችና በሴቶች ኢትዮጵያዊያኑ አሸነፉ


     በአለማችን ውዱ የዱባይ የማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶችን የሚያቆማቸው አልተገኘም፡፡ የሽልማት ገንዘብ እና በአለም ላይ ካሉ ትልልቅ ውድድሮች ሜዳማ የሆነው የዱባይ ማራቶን ዛሬ ማለዳ የተደረገ ሲሆን ኢትዮጵያዊው ፀጋዬ መኮንን 20432 በሆነ ሰአት በማሸነፍ 4 ሚሊየን ብር ሽልማት አሸናፊ ሆነ፡፡ 

        በውድድሩ በወንዶች ኢትዮጵያዊን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ተከታትለው ገብተዋል፣ ማርቆስ ገነቴ ሁለተኛ፣ ግርማይ ብርሀኑ ሶስተኛ፣ ታምራት ቶላ አራተኛ፣ አዝመራው በቀለ አምስተኛ ወጥተዋል ፡፡ 

     በዱባዩ ልዑል ሼክ ሀምዳን ቢን መሀመድ ቢን ራሺድ አል መክቱም የበላይ ጠባቂነት በተደረገው የአለማችን ውዱ ውድድር 20 ሺህ አትሌቶች ተሳትፈውበታል፣ በሴቶቹም ምድብ ከአንደኛ እስከ ዘጠነኛ ተከታትለው ገብተዋል ፡፡  

 

     በቀዳሚነት ሙሉ ሰቦቃ 22501 ስተገባ መሰለች መልካሙ 22523 ሁለተኛ ፍሬህይወት ዳዶ 22553 ሶስተኛ ሲወጡ እስከ ዘጠነኛ ደረጃ ያለውንም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተከታትለው ገብተዋል ፡፡  ዘጠነኛ ላይ ቱርካዊቷን አትሌት ተከትለውም ከአስረኛ እስከ አስራ ስድስተኛ ደረጃን ይዘዋል ፡፡                                                                                                                                                            

                                 ምንጭ ፦ gulfnews.com እና ድሬ ቲዩብ


No comments:

Post a Comment