Thursday, January 2, 2014

ፌዴሬሽን ምክር ቤት በአቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይ ላይ ውሳኔ አስተላለፈ ::

አቶ መላኩ የሞገቱበት የአዋጅ አንቀጽ እንዲስተካከል ተወሰነ ::

       በሙስና ወንጀል የተከሰሱት አቶ መላኩ ፈንታን ክስ መመልከት ያለበትን ፍርድ ቤት በሚመለከት ዛሬ የተወያየው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ክሱ መታየት ያለበት በጠቅላይ ፍርድ ቤት መሆኑን ለማሳየት ተከሳሹ የጠቀሱት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8 ንኡስ አንቀጽ 1 ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጣረስ በመሆኑ ከሕገ መንግሥቱ ጋር እንዲጣጣም ሆኖ እንዲስተካከል በአብላጫ ድምፅ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ ውሳኔው ስምንት ተቃውሞና ሁለት ድምፀ ተአቅቦ ተመዝግቦበታል፡፡

        የአዋጁ ንኡስ አንቀጾች እንደሚያስረዱት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በሥልጣን ላይ ሳሉ ከሥራቸው ጋር በተያያዘ በሚያጠፉት ጥፋት የሚጠየቁት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው፡፡ ነገር ግን ዛሬ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያደረገው  ውይይት  ባለሥልጣናቱ  በዚህ መልኩ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚጠየቁ  ከሆነ  ጥፋተኛ ወይም  ነፃ ቢባሉ  እነሱ ወይም መንግሥት  ይግባኝ  የሚሉበት   ዕድል አይኖርም፡፡  ይህ  ደግሞ  ሁለቱንም  ወገን  የሚጎዳና  የይግባኝ  መብትን  የሚፃረር  ነው፡፡

   ፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ  ባስተላለፈው  ውሳኔ መሠረት  የአቶ መላኩ  ክስ  በጠቅላይ  ፍርድ ቤት የመታየት  ዕድል  አይኖረውም፡፡

No comments:

Post a Comment