Wednesday, July 31, 2013

ቀን የጣለ እንደሆነ !



ገና ለሚመጣ ለማታው እንግዳ
እንዳትዘነጊ አለብን ፍሪዳ !

አንተ ያውድማ ቅራተኛ
ተጠንቀቅና ነቅተህ ተኛ
ታስወስዳለህ ምርትህን
ያፍሰዋልና ምርትህን !

ሰው አይቸገርም ሌሊት ዝናብ ቢጥል
ጉዳት የሚበዛው ቀን የጣለ እንደሆነ !
                                    

                                     ከቅኔ ማህደር

Thursday, July 25, 2013

ተወልደ ገብረማሪያም የ2013 የአየር መንገድ ስተራቴጂ ሽልማትን አሸነፉ

ሃምሌ 11 ፣ 2005

     የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም  አየር መንገዱ ቀጠናዊ ትስስሩን በማስፋት ለተጫወቱት ሚና  የአየር መንገድ ክልላዊ አመራር ሽልማትን አሸነፉ፡፡
     ዋና ስራ አስፈፃሚው ሽልማቱን በአለም አቀፍ አየር በረራ  ዘገባ ከሚሰራውና ቀዳሚ የአቬየሽን መፅሄት ከሆነው ኤር ላይን ቢዝነስ  ተቀብለዋል፡፡ሽልማቱ አንዱን የአለማችን ክፍል ከሌላው ጋር በአየር ትራንስፖርት ጠንካራ ትስስር እንዲኖረው አመራር ለሰጡ የሚበረከት ነው፡፡

    ሽልማቱ ከ8 ሺህ በላይ የሚሆኑት የአየር መንገዱ ሰራተኞች ታታሪነትና ጠንክሮ የመስራት ውጤት መሆኑን የሚያሳይ መሆኑን ሽልማቱን በተቀበሉበት ወቅት ተናግረዋል፡፡ ለድርጅቱ ሰራተኞች ምስጋናቸውን ያቀረቡት ዋና ስራ አስፈጻሚው ፥ ሽልማቱ አየር መንገዱ እ.ኤ.አ በ2025 ለማሳካት የወጠነው ራዕይ ስኬታማ እየሆነ መምጣቱን አመላካች እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

    አየር መንገዱ በ2025 ፍኖተ ካርታው 7 ራሳቸውን የቻሉ የስራ ክፍሎችን በማቋቋም በአመት 10 ቢሊዮን ዶላር ገቢ የማስገኘት ራዕይ ይዞ እየሰራ መሆኑን ከአየር መንገዱ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
 
                                                          ምንጭ  ፡-  ፋና ኤፍ ኤም 98.1
                                                    

Friday, July 19, 2013

የ12ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ሆነ


ሃምሌ 12 ፣ 2005

          የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተናን ከወሰዱ አጠቃላይ  ተማሪዎች መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ከ350 በላይ ነጥብ ማስመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ ተናገረ ።
        
  የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን ዱሬሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ፥ የተመዘገበው ውጤት ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ7 በመቶ ብልጫ አለው። በዘንድሮው ፈተና ከፍተኛ ውጤቶች የተመዘገቡት በመንግስት ትምህርት ቤቶች ሲሆን ፥ ከአምቦ ከተማ 637 በመሆን የተመዘገበው ደግሞ ከፍተኛው ውጤት ነው።
በፈተናው ተመሳሳይ ውጤቶች ያልተመዘገቡ ሲሆን ፥ ይህም ከኩረጃ የጸዳ የፈተና ስርአት መኖሩን እንደሚያሳይ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የዩኒቨርሲቲዎች መግቢያ ነጥብ በቅርቡ ይገለጻል ያሉት ዳይሬክተሩ ፥ ተማሪዎች ያመጡትን ነጥብ www.nae.gov.et ላይ እንዲሁም በሞባይል ስልኮቻቸው አማካኝነት በጽሁፍ መልዕክት መላኪያ በመግባት RTW ብለው በመጻፍ  የፈተና ቁጥራቸውን በማስገባት እና በ8181 የጽሁፍ መልዕክት በመላክ ማየት እንደሚችሉም ነው የተናገሩት።

                                                                             Source   : - Fana Fm 98.1

Wednesday, July 17, 2013

Marathon runner Meskerem Legesse Died Suddenly

Published: Jul 17, 2013 


HAMDEN, CT (WFSB) - Hamden emergency crews were able to deliver a baby after her mother, who ran in the 2012 Olympics for Ethiopia, passed away Monday afternoon.

Professional marathon runner Meskerem Legesse, 26, of Westport, was eating lunch at the Chinese restaurant in the 900 block of Dixwell Avenue when she suddenly collapsed on the floor, friends told Eyewitness News.

Emergency crews performed CPR on Legesse, who was three weeks away from delivering her second child. She was taken Yale-New Haven Hospital.

Legesse died a short time later; however, the baby was delivered by hospital staff.

Legesse's friends told Eyewitness News she was a professional marathon runner from Ethiopia but had to stop when she developed heart problems.

They said she was so careful with her second pregnancy, she only drank water.

"She always tried to eat healthy and she always makes sure her son eats good," said friend Fatima Sene. "I just don't know what to say."

Eyewitness News was told she had not been back to Ethiopia for nine years and was waiting for the birth of her second child so she could finally visit.

"She wanted to see her mother, so I want to get her home," Sene said. "I want to make sure she goes home."

Friends said Legesse also has a 2-year-old son. Both children are now being cared for by their father.



                             Source - Dire Tub

Sunday, July 14, 2013

በቻን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዋልያዎቹ ሩዋንዳን አሸነፉ


              ሃምሌ 7 ፣ 2005

    ቻን በሀገር ውስጥ የሊግ ውድድር የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በሚቀጥለው አመት በደቡብ አፍሪካ ለሚካሄደው 3ኛው የቻን አፍሪካ ዋንጫ 16 ሀገራት ይሳተፋሉ።
     የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደቡብ አፍሪካ ላይ በድጋሚ ለመገኘት የማጣሪያ ጨዋታዎቹን እያደረገ ሲሆን ፥ ቡድኑ በቅድመ ማጣሪያ ከኤርትራ ጋር ተደልድሎ ኤርትራ ራስዋን በማግለሏ  ምክንያት በፎርፌ ለቀጣዩ ጨዋታ አልፏል።

      ዛሬ ከቀኑ 10 ሰአት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የአንደኛ ዙር የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታ ዋልያዎቹ  የሩዋንዳ አቻውን በአስራት መገርሳ ጎል 1 ለ 0 አሸንፈዋል ።