Tuesday, January 28, 2014

ኢትዮጵያ ለሞሮኮው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ተካተተች፡፡


  በ2013 የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው ኢትዮጵያ ወደ 2015 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በሚደረገው የማጣሪያ ውድድር ካለ ቅድመ - ማጣሪያ ምድብ ውስጥ ተካታለች፡፡
 51 ሀገራት  የማጣሪያ ጨዋታ  በማድረግ ለሞሮኮው የአፍሪካ ዋንጫ 16 ብሄራዊ ቡድኖች የሚለዩ ይሆናል፡፡ጅቡቲና ሶማሊያ ዝቅተኛ በካፍ ደረጃ ዝቅተኛ ነጥብ በማገኘታቸው ከወድሁ የማይሳተፉ ሀገራት ሆነው ተለይተዋል፡፡
   የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን /ካፍ/ ባወጣው ድልድል መሰረት ኢትዮጵያን ጨምሮ 21 ሃገራት ምድቡን ተቀላቅለዋል፡፡ ካፍ የቅርብ ጊዜ ውጤቶችን ተንተርሶ  ባወጣው ደረጃ መሰረት ኢትዮጵያ 16ኛ ደረጃን መያዟ በቀጥታ ወደ ምድብ ማጣሪያው እንድትገባ ረድቷታል፡፡
በቅድመ ማጣሪያው 31 ሀገራት የሚሳተፉ ሲሆን 7 ሀላፊ ሀገራት  ወደ ምድብ ድልድሉ የሚያልፉ ይሆናል፡፡ 28 ሃገራት 7 ምድብ የሚከፈሉ ሲሆን ሚያዚያ 20 /2006 / ካይሮ በሚገኘው የካፍ ፅህፈት ቤት  የምድብ ማጣሪያ ድልድሉ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
   

      

No comments:

Post a Comment