Tuesday, January 21, 2014

የዓለም ኮከቡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የፓርቱጋልን የክብር ሜዳልያ ተሸለመ


 የ2013 የዓለም ኮከብ ተጨዋች ክብርን ከሳምንት በፊት በፊፋ የተቀናጀው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለፖርቱጋል ጀግኖች የሚበረከተውን የንጉስ ሄነሪ ሽልማት ጥር 12/2006 በሊዝበን ተበርክቶለታል፡፡ 

 
የሪያል ማድሪዱ እና የዓለም ኮከቡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በፖርቱጋል ቤተመንግስት በመገኘት ከፖርቱጋል ፐሬዝዳንት  አኒባል ኬባኮ  ሲልቫ እጅ  ሜዳሊያና ሪቫን ተቀብሏል፡፡
ሽልማቱ ለክለቤና ለሀገሬ የበለጠ ጠንክሬ በመስራት ብዙ ድሎችን እንዳገኝ ያበረታታኛል ሲል ሮናልዶ ከሽልማቱ በኋላ ተናግሯል፡፡
 የ28 ዓመቱ ሮናልዶ የዓለም ዋንጫን ከሀገሬ ጋር ማንሳት ህልሜ ነው ይህም የእግር ኳስ ህይወቴ ታላቁ ግብ ይሆናል በማለት ገልጧል፡፡ የፖርቱጋሉ ፐሬዝዳንት አኒባል ኬባኮ ሲልቫ በበኩላቸው ሮናልዶ ይህ ክብር ይገባዋል ምክንያቱም ሀገሩን ለዓለም ህዝቦች በሚገባ አስተዋውቋልና ብለዋል፡
  ሮናልዶ የዲስፕሊን፣ ጠንካራ የስራ ባህሪና የማሸነፍ ወኔ ባለቤት መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡ በሽልማቱ ስነ ስርዓት ላይ የሮናልዶን ቤተሰቦች ጨምሮ፣ የስፔን አምባሳደሮች፣ የሪያል ማድሪድ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ፣ የፖርቱጋል አሰልጣኝ ፓውሎ ፔንቶ እና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡

                                                                                         ምንጭ:  foxsports.com

No comments:

Post a Comment