Saturday, January 18, 2014

አዲሱ የግብጽ ህገ - መንግስት ኢትዮጵያ በአባይ እንዳትጠቀም የሚከለክል አንቀጽ ይዟል።

  በቅርቡ ሥራ ላይ የሚውለው አዲሱ የግብጽ ህገመንግስት ኢትዮጵያ በአባይ እንዳትጠቀም የሚከለክል አንቀጽ መያዙን አስመልክቶ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር “ተቀባይነት የሌለው” ሲል ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡ 

   የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ፣ “የግብጽ ህዝብ የራሱን ህገመንግስት የማውጣት መብቱን እናከብራለን፣ ነገር ግን የአንድ ሀገር ህገመንግስት የሌሎችን ሀገራት ጥቅም መጉዳት የለበትም” ብለዋል፡፡ 

     የግብጽ መንግስት በአባይ ወንዝ ለመጠቀም ቁርጠኛ ነው፣ የግብጽን ʻታሪካዊʼ መብቶች ያስጠብቃል የሚለው አንቀጽ ከኢትዮጵያና ከሌሎች የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት አቋም ጋር እንደሚጋጭ በግልጽ የሚታይ ሲሆን፣ ዲና ሙፍቲ በግብጾች ዘንድ ʻታሪካዊʼ የሚባለው መብት ኢትዮጵያ ያልፈረመችውና ያልተስማማችባቸው የቀኝ ግዛት ውሎች መሆናቸውን ጠቅሰው አብራርተዋል፡፡

                                                                         ምንጭ ፡- ድሬ ቲዩብ    

No comments:

Post a Comment