Sunday, December 21, 2014

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፓ ሕብረትን የደህንነት ማረጋገጫ አገኘ፡፡


   አዲስ አበባ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት ማስተላለፊያ (cargo hub) የአውሮፓ ሕብረትን የደህንነት ማረጋገጫ ማግኘቱን ገልጿል፡፡አየር መንገዱ በዚህ አሁን ባገኘው ACC3 በተባለው የደህነት ማረጋገጫ አማካኝነት ለቀጣይ አምስት አመታት እስከ 2019 ድረስ ያለምንም እክል ወደ አውሮፓ ሀገራት የጭነት በረራዎችን እንደሚያካሂድ አስታውቋል፡፡
 
  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘውን ይህን በገለልተኛ ተቋም የተረጋገጠ የደህንነት ማረጋገጫ ያላገኙ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አየር መንገዶች ወደ አውሮፓ እንዳይበሩ ሊታገዱ እንደሚችሉና በፍጥነት ማረጋገጫውን እንዲያገኙ ዓለማቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማሕበር አስታውቋል፡፡

No comments:

Post a Comment