Thursday, January 31, 2013

UNICEF Ethiopia appointed young humanitarian Hannah Godefa, a citizen of Canada with Ethiopian origin, as its Ambassador at a signing ceremony held in its premises on January 4.

15 year old Hannah involved in humanitarian activities when she visited her native land, Ethiopia, for the first time. Coming from Canada, Hannah got her inspiration when she interacted with local girls from the countryside who lack access to basic education materials.

''Even though I was happy to see my extended family, I was also very sad to see children my age that do not get much food, medicine, quality education and orphaned due to HIV and AIDS.” said Hannah.

Thursday, January 24, 2013

የጓሳ ጥብቅ ስፍራ እና መስህቦቹ….

 በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ውስጥ የምትገኘው ጓሳ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምሥራቅ 180 ኪሜ ላይ ትገኛለች፡፡ ከባሕር ወለል በላይ 3417 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘዋን ከፍተኛ ደጋማ ቦታ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመሆን እየሠራ የሚገኘው ፍራንክፈርት ዚኦሎጂካል ሶሳይቲ ነው፡፡ ተቋሙ በማኅበረሰብ ተኮር የቱሪዝም አካባቢ ጥበቃ ላይ በመሥራት ይገኛል፡፡ የፍራንክፈር ዚኦሉጂካል ሶሳይቲ የኢትዮጵያ ተወካይ / ዘላለም ተፈራ እንደተናገሩት፣ መጠሪያ ስሟን ‹‹ጓሳ›› ከሚባል ተክል ያገኘችው ጓሳ ብርቅዬ አዕዋፋትና የዱር እንስሳት የሚገኙባት፣ የመንዝ ጥንታዊና ባህላዊ የቤት አሠራር ሥነ ሕንፃ የሚታይባት፣ ከጓሳም ሆነ ከሌላ ቁስ የሚሠሩ ዕደ ጥበባት የሚገኝባት ናት፡፡ የጓሳ አካባቢ በኢትዮጵያ ብቻ ከሚገኙ አጥቢ እንስሳት 23 በመቶ የሚሆኑት የሚገኙበት ብርቅዬውን የኢትዮጵያ ተኩላ በቅርበት ለማየት የሚቻልበት፣ የጭላዳ ዝንጀሮም መናኸሪያ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት 861 የወፎች ዝርያዎች 114 ይገኙበታል፡፡ ፍራንክፈርት ዚኦሎጂካል ሶሳይቲ የአካባቢው ኅብረተሰብ ባሉት የመስህብ ቦታዎች ተጠቃሚ የሚሆንበትን ቦታውም የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን የጓሳ ማኅበረሰብ ሎጅ በስፍራው በማቋቋም እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡  ጓሳ የሚገኝበት የመንዝ- ጌራ ወረዳ ከተማ የሆነው መሐል ሜዳ ከአዲስ አበባ 282 . ርቀት ላይ ይገኛል፡፡


ከአዲስ አበባ ወደ ጓሳ ሲኬድ መተላለፊያው መዳረሻው ላይ በምትገኘው ይገም መንደር (ከጓሳ ሎጅ 12 . ርቀት ላይ የምትገኝ) በታሪካዊው አርባራ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ያልፈረሱ አጽሞችም ይታዩበታል፡፡ ‹‹ካለን የተፈጥሮ መስህብ ሀብት በተጨማሪ ትሁትና እንግዳ ተቀባይ ሕዝብ፣ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል የመረጃ ማዕከልና ሎጅ ለመጓጓዣ የሚጠቅሙ በቅሎና ፈረስ፣ የጎብኝዎችን ፍላጎት ሊያሟሉ የሚችሉ በአካባቢው ቁሳቁስ የተሠሩ የዕደ ጥበብ ውጤቶች አሉንና ኑና ጎብኙን፡፡