Monday, September 28, 2020

ኩናማዎች እና ባህላዊ እሴታቸው…..

 

የኩናማ ብሄረሰብ በ4 ትውልድ ሀረግ የተከፈለ ሲሆን እነሱም ጉማ፣ ካርዋ፣ ሸዋ እና ሴማ በመባል ይታወቃሉ፡፡ 4ቱም የዘር ሀረጎች ብሄራቸው እና ቋንቋቸው አንድ ቢሆንም እያንዳንዳቸው የሚለዩበት እና የራሳቸው የሆኑ ባህል አላቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የቤት አሰራር ጥበባቸው ነው፡፡

 ለአብነት ቤት አናት ላይ “ቡ” የመሰለ የፊደል ቅርፅ ያለው በትር ከተሰቀለ ዝርያው ከጉማ ነገድ መሆኑ በብሄረሰቡ ዘንድ በግልፅ ይታወቃል፡፡ ሌላው ሁለት የተጣበቁ “ቦ እና ባ” የመሳሰሉ በትሮችን በቤቱ አናት ላይ ከሰየመ ዝርያው የሴማ ነገድ መሆኑን ይረዳሉ፡፡ የካርዋ ነገድ ዝርያዎች ደግሞ ወደላይ የወጣ ዘንግ ቤታቸው አናት ላይ ሲሰቅሉ ፤ የሸዋ ነገድ አባላት በቤታቸው አናት ላይ አጭር ዘንግን በመሰየም የዘር ሀረጋቸውን ያመለክታሉ፡፡


 በዚህ መልኩ ከሩቅ የኩናማ መኖሪያ አካባቢ የመጣ የብሄረሰቡ አባል በእያንዳንዱ ቤት ላይ ያለውን ምልክት እያየ እንደ ነገዱ ዝርያ በቀጥታ ቤት ገብቶ ይስተናገዳል፡፡ በቦታ ርቀት ተለያይተው የሚኖሩ ተመሳሳይ ዝርያ ያላቸው ኩናማዎች ባይተዋወቁም አንድ ነገድ በመሆናቸው ብቻ እንደሚተዋወቁ ሆነው በፍቅር ያላቸውን ተካፍለው በእንግድነት ይስተናገዳሉ፡፡ 

 

 

Wednesday, September 23, 2020

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም እና ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊክንድ) የ2020 የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

የዘንድሮው ብሪጅ ሜከር አዋርድ አሸናፊ የሆኑት / ቴድሮስ አድሃኖም ከታይም መጽሔት 2020 የዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ 100 ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካትተዋል።


የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ / ቴድሮስ ከዓለማችን 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች መካከል አንዱ ሆነው ሊመረጡ የቻሉት በተለይ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ሁሉም ሰው እኩል የጤና አገልግሎት ተደራሽነት እንዲያገኝ በያዙት ጠንካራ አቋም ነው ተብሏል። በተጨማሪም፣ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ ለመከላከል በተደረገው ጥረት የራሳቸውን አበርክቶ ማድረጋቸውም ተጠቃሽ ነው።


/ ቴድሮስ አድሃኖም 2020 ብሪጅ ሜከር አዋርድ ሽልማታቸውን በትላንትናው እለት የተቀበሉ ሲሆን ሽልማቱ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ግንባር ቀደም ሆነው እያገለገሉ ላሉ የጤና ባለሙያዎች መታሰቢያ ይሁንልኝ ሲሉ የምስጋና መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሌላኛው ተፅዕኖ አሳዳሪ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የካንዳ ዜግነት ያለው አቤል ተስፋዬ ( ዊክንድ) በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳጅነትን እያተረፈ የመጠ ድምፃዊ፣ ገጣሚ እና የሙዚቃ ፕሮዲውሰር ነው። አቤል ተስፋዬ ( ዊክንድ) 2020 በለቀቀው after hours በተሰኘ የሙዚቃ አልበም ተወዳጅነት ማግኘቱ የተነገረ ሲሆን በተለይ Blinding Lights ሙዚቃው 2020 በፖፕ ሙዚቃ ዘርፍ ተመራጪ መሆኑን መረጃዎቹ ያመለክታሉ።

                                   ምንጭ ፡- ኢ.ቢ.ሲ እና ኤፍ.ቢ.ሲ