Tuesday, January 21, 2014

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አነስተኛ አውሮፕላኖችን ለመግዛት አቅዷል፡፡


       እ.ጎ.አ በ2025 ትርፉን አምስት እጥፍ አሳድጎ 10 ቢሊየን ዶላር ለማትረፍ ያቀደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ1 እስከ 2 ቢሊየን ዶላር በሚሆን ወጪ ከ10 እስከ 20 የሚደርሱ አነስተኛ አውሮፕላኖችን ለመግዛት አቅዷል፡፡
   

  አየርላንድ ደብሊን ላይ በተካሄደው የአየር መንገዶች የኢኮኖሚ ኮንፈረንስ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ (CEO) የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ባለፈው ዓመት በባትሪ ችግር ስራ አቁሞ ስለነበረው የቦይንግ ምርት የሆነው ድሪም ላይነር አውሮፕላኖችም አስመልክቶ፣ “በባትሪው ላይ ምንም አይነት ችግር አጋጥሞን አያውቅም” ብለዋል፡፡


 
     የኢትዮጵያ አየር መንገድ 5 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች ያሉት ሲሆን ባለፈው ዓመት አንደኛው በለንደን የሂትሮው አውሮፕላን ማረፊያ በተቀመጠበት በእሳት ተያይዞ በቅርቡ ታድሶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት ንብረትነቱ የጃፓን አየር መንገድ የሆነው ድሪምላይነር አውሮፕላን በበረራ ላይ እያለ ነጭ ጭስ ሲወጣው በመታየቱ እንዲያርፍ መደረጉ ታውቋል - የአውሮፕላኑ ባትሪም የመቅለጥ ባህሪ እንዳሳየም ተዘግቧል፡፡

                                                                                                         ምንጭ ፡- ድሬ ቲዩብ

No comments:

Post a Comment