Thursday, January 29, 2015

የሌ/ጀኔራል ጃገማ ኬሎ 94ኛ ዓመት የልደት በዓል ትላንት ተከበረ


  በጣሊያን ዳግም ወረራ ወቅት 15 አመታቸው ከፋሽስት ወራሪ ጦር ጋር በተለያዩ አውደ ግንባሮች ተፋልመው ከፍተኛ ጀብዱ የፈፀሙት እና ጣሊያን ከአገር ተሸንፎ ከወጣ በኋላም የአገር ዳር ድንበርን በማስጠበቅ ከፍተኛ ጀግንነት የፈፀሙት የሌ/ጀኔራል ጃገማ ኬሎ 94 የልደት በዓል ትላንት ጥር 20 ቀን 2007 .. ተከብሯል፡፡


  በ1929 . ጣሊያን  40 ዓመታት የአድዋ ሽንፈት በኋላ  ዳግም ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ገና 15 ዓመት ወጣትነት ዕድሜያቸው የራሳቸውን ጦር በማደራጀት ጠላትን የተዋጉት /ጀኔራል ጃገማ ኬሎ በወቅቱ በተለያዩ የጦር ውሎዎች በጠላት ላይ ከፍተኛ ጀብዱን ተቀዳጅተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ሶማሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት የአገርን ዳር ድንበር በማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡


  ሌ/ጄኔራል ጃገማ ኬሎ ጥር 20 ቀን 1913 .. የተወለዱ ሲሆን፤ በትላንትናው ዕለት ቀበና አካባቢ በሚገኘው የልጃቸው የትምወርቅ ጃጋማ ቤት የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት 94 አመት የልደት በዓላቸውን አክብረዋል፡፡ /ጀኔራል ጃገማ ኬሎ በአጼ ኃይለስላሴ ዘመን ከነበሩት ጀኔራሎች መካከል በአሁን ወቅት በህይወት ከሚገኙት ሁለት ጀኔራሎች (በውጭ ሀገር የሚገኙት /ጀኔራል ወልደስላሴ በረካ እና ሀገር ውስጥ ያሉት 94 ዓመቱ /ጀኔራል ጃገማ ኬሎ) አንዱ ሲሆኑ፤ጀኔራሉ አንድ ወንድና አምስት ሴት ልጆች፣ አምስት የልጅ ልጆችና አራት የልጅ ልጅ ልጆችን አፍርተዋል፡፡


 /ጀኔራል ጃገማ ኬሎ በህይወት እያሉ በደራሲ ፍቅረ-ማርቆስ ደስታጃገማ ኬሎ የበጋው መብረቅ” በሚል የህይወት ታሪካቸው ተፅፏል፡፡ ሌ/ጀነራል ጃገማ 15 አመት ዕድሜያቸው ወራሪውን የጣሊያንን ጦር ለመዋጋት ከዘመቱበት የአርበኝነት ገድል ጀምሮ እስከ መደበኛው የሀገሪቱ መካላከያ ጦር ድረስ ለኢትዮጵያ እና ለህዝቧ ነፃነት እና ክብር ሲሉ በርካታ የጦር ገድሎችን መፈፀማቸው ይታወቃል፡፡

Wednesday, January 21, 2015

የሚሊዮኖች ተስፋ…….. የአለም ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ


 1987 - 2009(..) ካሉት የአለም የምግብ ተሸላሚዎች ውስጥ ከፍተኛውን ደረጃ ይዘው የሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ እና የህንድ ተመራማሪዎች ናቸው፡፡ 2009 ደግሞ ኢትዮጵያ በፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ የአለምየምግብ ሽልማትን አግኝታለች፡፡ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ ድርቅን እና አቀንጭራን የሚከላከለውን የማሽላ ዝርያ አግኝተዋል፡፡  2009 የአለም የምግብ ሽልማት ድርጅት /FAO/ ተሸላሚ ሲሆኑ በምርምር
 ውጤታቸውም በአለም ላይ ከግማሽ ቢሊዮን በላይ የሚሆኑ ህዝቦችን ተጠቃሚ አድርገዋል፡፡


 ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዲስ ለተቋቋመው የሳይንቲስቶች አማካሪ ቦርድ አባልነትም ተመርጠዋል፡፡ ፕሮፌሰር ገቢሳ 26 አባላትን ላካተተው የተባበሩት መንግስታት የሳይንቲስቶች አማካሪ ቦርድ ሲመረጥ ብቸኛው የእርሻ ሳይንቲስት እንደሆኑ የተለያዩ አለም አቀፍ የብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡ ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ በአለም አቀፍ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል፡፡ ከአለም የምግብ ሽልማት ድርጅት የተሰጣቸውን 250,000 ዶላር እና ሌላ ገንዘብ በማሰባሰብ ፋውንዴሽን ለማቋቋም አስበዋል፡፡

  
   የአለም ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ የምርምር ውጤት የሆነው የማሽላ ዝርያ ከሰሃራ በታች ለሚገኙ አገራት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያስቻለ ይገኛል፡፡ ይሄው የማሽላ ዝርያ ምርቱ ከፍተኛ ፣ በንጥረ ነገር የበለፀገ እንዲሁም ድርቅ ፣ ውርጭ ፣ ተባይ ፣ በሽታ እና አቀንጭራን የመቋቋም አቅም አለው፡፡ 


  ሎሬቱ በፐርዱ ዩኒቨርስቲ የእፀዋት ማራባት ፕሮግራም ድርቅን እና አቀንጭራን የሚቋቋሙ ብዙ የማሽላ ዝርያዎችን አጥንተዋል፡፡ ይህም በፊት አርሶ አደሩ ይጠቀም ከነበረው ዝርያ በ10 እጥፍ ምርታማነትን ያሳድጋል፡፡ ድርቅ እና አቀንጭራን በመቋቋም ከፍተኛ ምርት ይሰጣሉ የተባሉት የማሽላ ዝርያዎችም ለሀገራችን አርሶ አደሮች ተሰራጭተው ውጤታማ ሆነዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የፕሮፌሰሩ አስተዋፅኦ የላቀ ነው፡፡


  ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ 1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አለም ፣ 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጅማ እርሻ ኮሌጅ አዳሪ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡ ከዚያም ትምህርታቸውን አጠናክረው በመቀጠልም “በፅዋት ሳይንስ” ከሀሮማያ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡ በሀሮማያ ዩኒቨርስቲ እየተማሩ እያለም የውጭ እድል አግኝተው በፐርዱ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ እና የሶስተኛ ዲግሪያቸውን /ፒኤች ዲግሪያቸውን/ አግኝተዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ ….. https://www.youtube.com/watch?v=QMMTMDq_SSg

Sunday, January 18, 2015

“ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ……..”

   

   በኢትዮጵያ አመታትን ጠብቀው የሚከበሩ ሀይማኖታዊ በዓላት ከእምነት ፋይዳቸው ባለፈ በውስጣቸው በያዙት መስህባዊ ተፈጥሮ ምክንያት በርካት የውጪ እና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን ይስባሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ደግሞ የጥምቀት በዓል ነው፡፡ የስነ መለኮት ምሁራን ጥምቀት ለሚለው ቃል መነከር ፣ መታጠብ ፣ መረጨት እና እና የመሳሰሉትን ትርጓሜዎች ይሰጡታል፡፡የጥምቀት ዋዜማ ከተራ ይባላል፡፡ የከተራ እለት/ ጥር 10 ማለት ነው/ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በሚሰማው የደውል ጥሪ ታቦታቱ ፤ የተለያዩ ህብረ ቀለማት ያላቸው አልባሳት በለበሱ ህዝበ ክርስቲያን ታጅበው ጉዞአቸውን ወደ ጥምቀተ ባህር ያደርጋሉ፡፡


  በሀገራችን ታቦት ተሸክሞ ፣ ወንዝ ወርዶ የክርስቶስን በዓለ ጥምቀት ማክበር የተጀመረው በአፄ ገብረመስቀል ዘመነ መንግስት እንደሆነ ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ ይህንን ታሪክ በመከተል አፄ ነዖድም(1486 - 1500 ዓ.ም) ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ ሁሉ ታቦተ ህጉን ወደ ጥምቀተ - ባህሩ በሚወርድበት ጊዜ እና ከጥምቀተ - ባህሩ ወደ ቤተ መቅደሱ በሚመለስበት ጊዜ  አጅቦ መውረድ እና መመለስ እንዳለበት አዋጅ አስረግረው ነበር፡፡ በአዋጁ መሰረትም ህዝቡ በየአመቱ ታቦተ ህጉን በማጀብ ወንዶች በጭፈራ እና በሆታ፣ ሴቶች ደግሞ በእልልታ ሲያከብሩ ኖረዋል ፤ አሁንም እያከበሩት ይገኛል፡፡
 
   
  በከተራው ዕለት ድንኳን ተተክሎ ፣ ዳሱ ተጥሎ እና ውኃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ፤ ታቦተ ህጉ የሚንቀሳቀስበት ሰዓት ሲደርስ የየቤተ መቅደሱ ታቦታት በወርቅ እና በብር መጎናፀፊያ እየተሸፈኑ ፤ በተለያየ ህብር በተሸለሙ የክህነተ አልባሳት በደመቁ ካህናት እና የመፆር መስቀል በያዙ ዲያቆናት ከብረው፣ ከቤተ መቅደስ ወደ አብሕርት/ መጥማቃት/ ለመሄድ ሲነሱ መላው አብያተ ክርስቲያናት የደውል ድምፅ ያሰማሉ፡፡ ምዕመናንም ከልጅ እስከ አዋቂ በአፀደ ቤተ ክርስቲያን እና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ እንደሚባለው ያማረ ልብሳቸውን ለብሰው በዓሉን ያደምቃሉ፡፡


  ታቦታት  ከቤተ መቅደሳቸው ወጥተው በህዘበ - ክርስቲያኑ ታጅበው ማደሪያ ቦታቸው ይደርሳሉ፡፡ በዚያን ጊዜ ዳቆናት እና ቀሳውስት በባህረ ጥምቀቱ ዙሪያ ሆነው ከብር የተሰሩ መቋሚያ እና ፅናፅን እንዲሁም ከበሮ ይዘው በነጫጭ እና በወርቅ ቀለም ባሸበረቁ እጥፍ ድርብ አልባሳት አምረው እና ተውበው፤የክርስቶስን የጥምቀት ታሪክ የሚያወሱ ወረብ እና መዝሙሮችን ጣዕም ባለው ዜማ ያቀርባሉ፡፡ ሌሊቱን ስብሀተ - እግዚአብሔር ሲደርስ አድሮ ከዚያም ስርዓተ ቅዳሴው ይፈፀማል፡፡ በወንዙ /በግድቡ/ ዳር ፀሎተ- አኩቴት ተደርሶ  4ቱ ወንጌላት ከተነበቡ በኋላ ባህረ ጥምቀቱ በብፁዓን አባቶች ተባርኮ ለተሰበሰበው ህዝበ - ክርስቲያን ይረጫል፡፡ ለዚህ በዓል ህዝበ ክርስቲያኑ ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል፡፡ ምክንያቱም በዓሉ እየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ተምሳሌት በማሰብ ስለሚከበር፡፡


የጥምቀት በዓል ሀይማኖታዊ ስርዓቱን ከባህላዊ ወግ እና ስርዓት ጋር አጣምሮ የያዠ ነው፡፡ በዚህም በርካታ ብሄር ብሄረሰቦች ህብረ - ቀለማዊ የሆነ ጨዋታቸውን በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ያቀርባሉ፡፡ በዓሉን ለማክበር ወደ ጥምቀተ ባህር የሚሄዱ ሰዎች ከበዓሉ በፊት ተዋወቁም አልተዋወቁም በዚያን ዕለት በጋራ ሆነው ጥዑም ዜማዎችን ያንቆረቁራሉ፡፡ ይህ ዕለት ማንም ሰው ሳያፍር እና ሳይሸማቀቅ የውስጡን የሚገልፅበት እና በጋራ የሚጫወትበት ዕለት ነው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በጓደኝነት ለመተጫጨት ለሚፈልጉ ወጣቶች መልካም አጋጣሚን ይፈጥራል፡፡ ህዝበ - ክርስቲያኑ ይህንን በዓል ዘር እና ቀለም ሳይለዩ በአንድነት ያከብሩታል፡፡ በመሆኑም በዓሉ ህዝብን ያቀራርባል፤ የመረዳዳት ባህልንም ያሳድጋል፡፡
  
     
   የጥምቀት በዓልን ለማክበር የተለያዩ ሀገር ዜጎች ዲፕሎማቶች፣ አምባሳደሮች እና ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም የቤተክርስቲያን አባቶች እና ምዕመናን ይታደማሉ፡፡ ይህ በዓል በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚከበር ቢሆንም በተለይ በአፄ ፋሲል መዋኛ በላልይበላ በመቀሌ በአክሱም እና በአዲስ አበባ ከተሞች በተዘጋጀላቸው የክብር ቦታ ዝበ - ክርስቲያኑ ከውጪ ከሚመጡ ቱሪስቶች ጋር በዓሉን በደመቀ ሁኔታ ያከብሩታል፡፡  ታዲያ በዚህ በዓል ላይ ያስገረማቸውን ነገር በማስታወሻነት ለማስቀመጥ የተለያዩ ሰዎች የፎቶ እና የቪዲዮ ካሜራዎቻቸውን ደግነው እያነሱ እና እየቀረፁ ያስቀራሉ፡፡


  በመጨረሻም በሀገራችን የሚከበሩ ሀይማኖታዊ በዓላት የመረዳዳት እና የመደጋገፍ ባህልን ያዳብራሉ፡፡ ከዚህም ባሻገር አገሪቱ ከቱሪዝም ኢንዱስትሪው ተጠቃሚ እንድትሆን ያስችሏታል፡፡ ስለዚህ ተገቢውን ትኩረት ልንሰጣቸው ይገባል፡፡