Tuesday, July 29, 2014

ልክ የዛሬ ዕለት ሀምሌ 22/1928 ዓ.ም ብፁዕነታቸው በሰማዕትነት አረፉ

   1875 ..በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰላሌ  አውራጃ ፍቼ  ከተማ ተወለዱ። ወላጆቻቸው ዕድሜያቸው  ገና በወግ ለትምህርት  ሳይደርስ  ወደ  ደብረ ሊባኖስ  ገዳም በመውሰድ  ባሕታዊ  ተድላ  ለተባሉ  መምህር  አደራ ሰጧቸው።   በዚያው  ገዳም  የንባብ  ቤቱን ና የዜማውን የትምህርት  ደረጃዎች  በሚያስገርም ሁኔታ  በአጭር  ጊዜ  አቀላጥፈው  በመጨረስ  ገና በልጅነት  የዕድሜ  ደረጃቸው  ሦስተኛውን  የቅኔ ትምህርት  ጀምረው  በአጭር  ጊዜ ሙሉ ቤት  ተቀኙ። ይህንኑ  የቅኔ  ትምህርት ለማስፋፋት በምዕራብ ጎጃም  ሀገረ ስብከት  ወደ ሚገኘው  የቅኔ ትምህርት  ማዕከል  ዋሸራ  ተሻግረው ለመምህርነት  የሚያበቃውን  ትምህርት ፈጽመው አስመሰከ።

   ከዚያም  ከቅኔው  ዓውድማ  ጎጃም  ወደ  ዜማው  አዝመራ  ጎንደር  ተሻገሩ።  በዚያም  እንደ  ቅኔው ሁሉ እስከ  ማስመስከር  ባይደርሱም  የዜማውን  ትምህርትበአጥጋቢ ሁኔታ ቀጠ።  ከጎንደርም በወቅቱ  ወሎ  ቦሩ ሜዳ  ከተባለው  ቦታ  ላይ  ወንበር  ዘርግተው  የመጻሕፍትን  ምሥጢር በየዓይነቱ  ሲመግቡ  ወደ  ነበሩት  ስመ ጥሩው  መምህር  አካለ ወልድ  ዘንድ  በመሔድ  ዋናዋናዎቹን  የመጻሕፍት  ትርጓሜ  ትምህርቶች  ማለትም ብሉያትን፣ ሐዲሳትንና ሊቃውንትን በብቃት ተከታተሉ 

  
ከዚህ  በኋላ  ልክ  1900 ..  እዚያው  ወሎ  አማራ ሳይንት  በተባለው  ቦታ  ወደሚገኘው ምስካ  ቅዱሳን ገዳም  በመሔድ  ወንበር  ዘረጉ።  በዚያው  ቦታ  ለዘጠኝ  ዓመታት  ያህል ቅኔንና መጻሕፍትን አስተማሩ። በዚህ  ዓይነት  በመማርና  በማስተማር  ራሳቸውን  በእግዚአብሔር  ቃል  በሚገባ  ከጐሰሙ  በኋላ 1909 .. ወደ  ደብረ  ሊባኖስ  ገዳም  በመሔድ 
ሥርዓተ  ምንኩስናን  ፈጸሙ።  ብዙም  ሳይቆዩ ማዕረገ  ቅስናን  ተቀብለው  ከወንበሩ  አገልግሎት  ጋር  የቤተ  መቅደሱን  ተልእኮም  ደርበው  ያዙ።

 በ1910 ..  መምህር  ኃይለ  ማርያም  ተብለው  በወላይታ  ሶዶ  በሚገኘው  ደብረ  መንክራት ምሁር  ኢየሱስ  ገዳም  ተሾሙ።  1916 ..  እንደገና  በዝዋይ  ደብረ  ምሕረት  ቅዱስ  ገብርኤልገዳም  በመምህርነት  ተሾሙ።  1919 ..  ወደ  አዲስ  አበባ  በመምጣት  የመንበረ  መንግሥት ቅዱስ  ማርቆስ  መምህርና  በቤተ  መንግሥት  የግርማዊ  ቀዳማዊ  ኃይለ ሥላሴ  አበ ንስሐ  ሆኑ።

 የግብፅ  ቤተ  ክርስቲያን  ከአንድ    ስድስት  መቶ  ዓመታት  በኋላ  የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ  ተዋሕዶቤተ  ክርስቲያን  በዕውቀት  መንፈሳዊ  ከእርሷ  ተወልው  በእቅፏ  ውስጥ  ባደጉ  ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት
 እንድትመራ ፈቃዷን  ስትገልጽ  ከተመረጡት  አባቶች  አንዱ  በመሆን  ግንቦት  18 ቀን1921 ..  በእስክንድርያው  መንበረ  ማርቆስ  ቤተ  ክርስቲያን  ማዕረገ  ጵጵስናን  ተቀበሉ። ከዓመት  በኋላም አቡነ  ጴጥሮስ  ጳጳስ  ዘምሥራቅ  ኢትዮጵያ  ተላዌ አሠሩ  ለአቡነ  ኢየሱስ ሞዓ ተብለው  በያኔው  መንዝና ወሎ አገረ ስብከት ተሾሙ። የኢጣሊያ ፋሺስት 1928 .. በኢትዮጵያ ላይ የግፍ ጦርነትን ባነሣ ጊዜ ብፁዕ አቡነጴጥሮስ ከጦር ስፍራ ለመለየት ስላልሆነላቸው፣ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ተከትለው ወደ ሰሜን ጦር  ግንባር  ዘምተዋል፡፡

ፋሺስቱ  በማይጨው የመርዝ  ጦርነት ከማድረጉ  የተነሣ፣ የኢትዮጵያ ሠራዊት  ሲበታተንም  ከንጉሠ  ነገሥቱ  ጋር  የተመለሱት  አቡነ  ጴጥሮስ  ወደ  ደብረ  ሊባኖስ  ሄደው ለአገርና  ለነፃነት  መሞት  ቅዱስ  ተግባር  መሆኑን  ለሥላሴ  አርበኞች በመስበክም ይታወቃሉ፡፡

    አርበኞች አዲስ  አበባን  በሁለት  አቅጣጫዎች  ከሰሜናዊ  ምዕራብ   እና  በደቡባዊ  ምሥራቅ  አቅጣጫ  ለመቆጣጠር  ውጊያ  በከፈቱበት  ጊዜ  የተማረኩት  አቡነ ጴጥሮስ፣  ለፋሺሽት  እንዲገዙ የኢጣሊያ  መንግሥት  ገዢነትንም  አምነው  አሜን ብለው  እንዲቀበሉ ግፊት  ቢያደርጉባቸውም፤እምቢኝ ለሀገሬና  ለሃይማኖቴ  ብለው  ለሰማዕትነት  ያበቃቸውን የሞት ጽዋ ተቀብለዋል፡፡ አቡነ ጴጥሮስ ከሚገደሉበት ስፍራ ሲደርሱ አራቱን ማዕዘን በመስቀላቸው ባረኩ፡፡ በህዝቡም ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፡፡ “ፋሽስቶች የአገራችንን አርበኞች ሽፍታ ቢላቸውም እውነት አይምሰላችሁ፡፡ ሽፍታ ማለት አለሀገሩ ሀገሩ መጥቶ የሰውን ሀገር የሚወር፣ ይህ በመካከላችሁ የቆመ አረመኔው ፋሽስት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ለእሱ እንዳይገዛ ውጉዝ ነው፡፡ የኢትዮጵያም መሬት እንዳትቀበለው የተገዘተች ትሁን፡፡” ብለው ተናገሩ፡፡
    ሐምሌ 22 ቀን 1928  ስምንት  ወታደሮች  በስተጀርባቸው  ሃያ  እርምጃ  ርቀው  ተንበርክከውበተንጠቀቅ  ቆሙ።  ወዲያው  አዛዡ  «ተኩስ»  በማለት  ትእዛዝ  ሲሰጥ  ስምንቱም  ተኩሰው መቷቸው።  ግን  በስምንት  ጥይት  ሳይሞቱ  ቀሩ።  መሞታቸውንና  አለመሞታቸውን  ለማረጋገጥ ዶክተር  ተጠራ።  ዶክተሩም እንዳልሞቱ  አረጋገጠ።  ከዚያም ሌላ  ወታደር  በሦስት የሽጉጥ  ጥይት ራስ  ቅላቸውን  መትቶ ገደላቸው።


  « እኔ ግን ኢትዮጵየዊ ነኝ፡፡ ሓላፊነትም ያለብኝ የቤተክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ
 ስለሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ፡፡. እኔን  ለመግደል  እንደወሰናችሁ  አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ  ላይ  የፈለጋችሁትን  አድርጉ፡፡ግን  ተከታዮቼን  አትንኩ» 
አኩሪ  በሆነ አባታዊ  ሓላፊነታቸው ለአገር፣ ለቤተክርስቲያን፣ ለወገን  ሁሉ አለኝታነታቸው አረጋግጠው ሐምሌ 22 ቀን 1928 ..  በሰማዕትነት  አለፉ፡፡
  


  የብፁዕነታቸውን አኩሪ ታሪክ ትውልድ ሲያዘክርላቸው እንዲኖርም መታሰቢያ ይሆናቸው ዘንድ ሐምሌ 16 ቀን 1938 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ እምብርት ሐውልት ቆሞላቸዋል። ምንም እንኳን  አሁን ለጊዜው ቢነሳም……..