Wednesday, January 22, 2014

ንብረትነቱ የዩክሬን የሆነ አንድ አንቶኖቭ አውሮፕላን ተከሰከሰ ፡፡


   ንብረትነቱ የዩክሬን የሆነ አንድ አንቶኖቭ አውሮፕላን ከኢንቴቤ ኡጋንዳ በኢትዮጵያ በኩል አልፎ ወደ የመን ሲያቀና ሰኞ እለት 3፡35 ላይ አዲስ አበባ አካባቢ ለገዳዲ ላይ ተከስክሷል፡፡

        የአውሮፕላኑ አብራሪዎች በኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ ለማለፍ ጠይቀው ተፈቅዶላቸው እየበረሩ አዲስ አበባ አካባቢ ሲደርሱ አውሮፕላኑ የሞተር ዕክል ገጥሞት የአደጋ ጊዜ ማረፍ (Emergency Landing) በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ሊያደርግ ሲያቆበቁብ ነበር ለገዳዲ አካባቢ የተከሰከሰው፡፡

   ይህ  የመንገደኛ  አውሮፕላን  ምንም ተሳፋሪ  እንዳልያዘና  በህይወት የተረፉት  አብራሪዎች ለህክምና  ወደ  ሆስፒታል  እንደተወሰዱ  ታውቋል፡፡

No comments:

Post a Comment