Sunday, August 21, 2016

የዘመን መለወጫ ዋዜማ … ሂሩት በቀለ …ትውስታ !!!


  ቀደም ባለው ጊዜ በሙዚቃው አለም የተሠማራ ሰው አዝማሪ ስለሚባል ብዙዎች ወደ ሙያው ለመግባት ይቸገሩ ነበር፡፡ ከቤተሰብም ውስጥ ልጆቻቸው አዝማሪ እንዳይባሉ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያደርጉ ነበር፡፡ ድምፃዊት ሂሩት በቀለም ይህንን ፍራቻ ቤተሰቦቿ ሳያውቁ 1 አመት ያህል ሠርታለች፡፡

  በ1951 . ተፈትና ምድር ጦር ኦርኬስትራ የተቀላቀለችው ሂሩት ለፈተና የተወዳዳረችበት ዘፈኗየሀር ሸረሪትይሰኛል፡፡ ይህንንም ዘፈን ከምድር ጦር ኦርኬስትራ ጋር በመሆን ለአዲስ አመት /ዘመን መለወጫ በዓል/ በብሄራዊ ትያትር መድረክ ላይ ተጫውታለች ይሁንና ከማፈሯ እና መደንገጧ የተነሳ ዘፈኑን ሳትጨርሰው ከመድረክ ወርዳለች፡፡ በኋላ ግን አሰገደች ካሳ ዘፈኑን እንደሷ አስመስላ ለታዳሚው ለመጫወት ሞክራለች፡፡

  በምድር ጦር ብዙም ሳትቆይ 1952 . ፓሊስ ሰራዊት ሙዚቃ ክፍል ገብታ በጡረታ እስከተገለለችበት ጊዜ ድረስ ለ30 ዓመትት ያህል አገልግላለች፡፡ አስገራሚ በሆነ ሁኔታም ፖሊስ ሰራዊት ሂሩትን ከምድር ጦር አስኮብልሏል፡፡ በጊዜውም ምድር ጦር ይከፈላት የነበረው ደሞዟ 60 ብር ሲሆን በፖሊስ ኦርኬስትራ 100 ብር አድጎላት ነበር፡፡ ከዚያን በኋላ በየዘመን መለወጫው ዋዜማ የበዓል ስራዎቿን በማቅረብ ከህዝብ አድናቆት እና አክብሮትን አግኝታለች፡፡ በፓሊስ ቆይታዋም በርካታ ካሰቶችን ሠርታለች፡፡ 


  ድምፃዊት ሂሩት በቀለ በግል ከሰራቻቸው ሙዚቃዎች ባሻገርም በጋራ የተጫወተቻቸው ጥቂት የማይባሉ ሙዚቃዎች አሏት፡፡ በአጠቃላይ በቆይታዎ ከምድር ጦር እና ፓሊስ ኦርኬስትራ እንዲሁም ዋልያስ ፣ ሮሃ እና ዳህላስ ባንዶች ጋር ስራዎቿን አቅርባለች፡፡ እዚሁ መዲናችን አዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው ድምፃዊት ሂሩት በቀለ አሁን ራሷን ከሙዚቃው አለም አግልላ ወደ መንፈሳዊ አለም ገብታለች ፡፡ 

Monday, August 15, 2016

12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ



  የ12 ክፍል አገራቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ዋና ዳይሪክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሄር አስታውቀዋል፡፡ ተማሪዎች ውጤታቸውን በኤጀንሲው ዌብሳይት www.neaea.gov.et ላይ Student result የሚለው ቦታ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ማየት ይቻላሉ፡፡ ውጤት ለማየት ሌላኛው አማራጭ ደግሞ በነፃ አጭር የፅሁፍ መልክት 8181 ላይ RTW ብለው በመፃፍ  እና ክፍተት በመተው (ስፔስ በማድረግ) የመለያ ቁጥራቸውን አስገብተው በመላክ ማወቅ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

  የዘንድሮው 12 ክፍል መግቢያ ፈተና በመሰረቁ ምክንያት በተሰጠው ልዩ ትኩረት ቀን ከለሊት በመሰራቱ  እና ኤጀንሲው ተጨማሪ 10 የማረሚያ ማሽኖች ገዝቶ ወደ ስራ በማስገባቱ ውጤቱን በአፋጣኝ ለማውጣት መቻሉን የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሺፋ ገልፀዋል፡፡

 ብሄራዊ ፈተናውን 246 ሺህ 570 ተፈታኞች የወሰዱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 50 በመቶዎቹ 350 እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል። 106 ተፈታኞች ደግሞ 600 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 21ዱ ሴቶች ናቸው። ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥቡ በቅርቡ ይፋ እንደሚሆንም ኤጀንሲው አስታውቋል።
  10 ክፍል ውጤትም ከሐምሌ 15 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ ይፋ እንደሚደረግም ለማወቅ ተችሏል፡፡ 10 ክፍል ውጤት 12ኞቹ የዘገየው የተፈታኞቹ ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ በመሆኑ ለማረም የበለጠ ጊዜ በመፍጀቱ እንደሆነ ነው አቶ ረዲ ያስታወቁት፡፡

Thursday, August 11, 2016

"ዘማቹ ጓዴ" …………… ፀሃዬ ዮሀንስ


    በ197 . መጨረሻ ላይ በአምባሣደር ቲያትር ቤት ተቀጥሮ መድረክ ላይ የተጫወተው "ማንበብ እና መፃፍ" የሚል ስራውን ነበር፡፡ ብዙዎች ይህንን የፀሃዬ ዮሀንስ የመጀመሪያ ስራ አድርገው ይቆጥሩታል ይሁንና እሱ ግን ከዚህ በፊት ብርሃን ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት እያለ የእድገት በህብረት መዝሙሮችን ይጫወት ነበር፡፡ ለአብነትም "ዘማቹ ጓዴ" የተሠኘውን መጥቀስ ይቻላል፡፡ "ማንበብ እና መፃፍ" የተሠኘው ዘፈን ግጥም ደራሲ ዳምጠው ሲሆን ዜማው የራሱ የፀሃዬ ዮሀንስ ነው ፡፡ የሀሣቡ መነሻ ደግሞ በጊዜው በአምባሣደር ትያትር ቤት በርከት ያሉ ያልተማሩ ሰዎች መኖር ነበር፡፡ ዘፈኑ ከመሠተረ ትምሀርት አዋጁ ቀደም ብሎ የተሠራ ቢሆንም ከአዋጁ በኋላ ግን ድምፃዊ ፀሃዬ ከፍተኛ ታዋቂነትን አግኝቶበታል፡፡


   ከአምባሣደር ትያትር ቤት ወደ ራስ ቲያትርም ተዛውሮ 1973 -1983 . ድረስ ያገለገለው ፀሃዬ ዮሀንስ በዚህ ቆይታው በርከት ያሉ ዘፈኖችን በካሴት አሣትሞ ለህዝብ አድርሷል፡፡ የመጀመሪያ ካሴቱ "ተይ ሙኒት" ሲሆን ፍንጭቷ፣ ብቸኝነቴን፣ ማን እንደ ሀገር፣ ያላንቺማ እረ ስንቱን ተባለ እንዴ ለትንሽ እና ሳቂልኝ እያለ ቀጥሎ በቅርቡም "የኔታ" የተሠኘ አልበሙን ጀባ ብሎናል፡፡

  
   በ1975 . አካባቢ "ፍንጭቷ" የተሠኘውን ስራውን በካሴት ሲያሣትም ብዙዎቹ የዘፈን ግጥም ድርሰቶች የጋዜጠኛ ልዑል አማራ ነበሩ፡፡ በተለይ "ፍንጭቷ" የተሰኘው ዘፈን ደራሲው የፃፈውፍንጭቱበማለት ራሱን ፀሃዬ ዮሀንስ መነሻ በማድረግ ነበር የሰራው፡፡ ፀሃዬ ግንፍንጭቱየሚለው ወደ "ፍንጭቷ" በመቀየር ተጫውቶታል ፡፡ ይህን ዘፈን በጣም እንደሚወደው ፀሃዬ ዮሀንስ በአንድ ወቅት ገልፆ ነበር፡፡ ለጎዳና ተዳዳሪዎችየጥቁር አበቦችየሚል ስራ የተጫወተው ፀሃዬ ዮሀንስ እናቱን በሞት እንዳጣም ለእናቱምትክ አልባ እናቴየተሰኘ ስራ ተጫውቷል፡፡ ለድምፃዊ ፀሀዬ ዮሀንስ እድሜ እና ጤና በመመኘት ቀሪውን እናንተ ጨምሩበት…….