Monday, September 14, 2015

ተዋናይት ሰብለ ተፈራ - (ከ1968 – 2008 ዓ.ም.)

         
    
   አርቲስት ሰብለ ተፈራ (‹‹እማማ ጨቤ›› - ‹‹ትርፌ›› ) አዲስ አበባ ከተ ወሎ ሠፈር (አይቤክስ ሆቴል አካካቢ) ግንቦት 18 / 1968.. ተወለደች፡፡በተወለደች 40 ዓመቷ መስከረም 3 ቀን 2008 .. 10 40 ላይ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወቷ አልፏል፡፡ ሰብለ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን መስቀል ፍላወር አካባቢ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ተማረች፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ደግሞ በንፋስ ስልክ አጠቃይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምራለች፡፡ 1984 . 16 ዓመቷ በክብር ዶክተር አርቲስት ተስፋዬ አበበ የትያትር ክበብ ሠልጥናለች፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአርቲስት ቴዎድሮስ ተስፋዬ ጋር ‹‹ጭንቅሎ›› የተሰኘውን ትያትርን ሠራች፡፡ 
  

ባለቤቷ ሞገስ ተስፋዬ እና ተዋናይት ሰብለ ተፈራ

   በወጋገን ኮሌጅ ብሉ ስካይ ካምፓስ ተምራ በትወና በዲፕሎማ ተመርቃለች፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትያትር ጥበብ ትምህርት ክፍል የዲግሪ ትምህርቷን እየተከታተለች ነበር፡፡አርቲስት ሰብለ 30 በላይ ትያትሮችን እንዲሁም 20 በላይ ፊልሞችን ተውናለች፡፡
ከተወነችባቸው ትያትሮች መካከል - አምታታው በከተማ፣ 12 እብዶች በከተማ፣ ጓደኛሞቹ ወርቃማ ፍሬ፣ ሰቀቀን ህይወት በየፈርጁ የሠርጉ ዋዜማ፣ ላጤ፣ እቡይ ደቀ መዝሙር አንድ ቃል፣ የክፉ ቀን ደራሽ፣ እንቁላሉ፣ አብሮ አደግ፣ ሩብ ጉዳይ፣ እና ሌሎችም ትያትሮች ይጠቀሳሉ፡፡ ከተወነቻቸው ፊልሞች መካከል ፈንጅ ወረዳ፣ ያረፈደ አራዳ፣ ትንቢት የሚሉት ፊልሞች ይገኙበታል፡፡በሀገረ እንግሊዝ፣ አሜሪካ እና በሌሎች አገራት ‹‹የእኛ እድር›› የሚለው ትያትር አቅርባለች፡፡ በእሥራኤል ‹‹ሴት ወንድሜ›› የተሰኘ ትያትር ይዛም ተጉዛለች፡፡
  

  በዮናስ አብርሃም ተደርሶና ተዘጋጅቶ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለአምስት ዓመታት በቀረበው ‹‹ ትንንሽ ፀሐዮች›› ተከታታይ የሬዲዮ ድራማ ‹‹እማማ ጨቤ›› ገፀ ባህርይን ወክላ ተጫውታለች ፡፡በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በቤቶች ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ቤት ሠራተኛዋን ‹‹ ትርፌ›› ገፀ ባህርይ ወክላ በመተወን ላይ ነበረች፡፡አርቲስት ሰብለ ‹‹አልበም ›› የተሰኘውን ፊልም አዘጋጅታለች፡፡ ‹‹እርጥባን›› በተሰኘው ትያትር በአዘጋጅነት ሠርታለች፡፡ በርካታ የሬድዮና የቴሌቪዥን ማስታወቂዎች በመሥራት ላይ ነበረች፡፡አርቲስት ሰብለ ተፈራ ከአቶ ሞገስ ተስፋዬ ሚያዝያ 27 ቀን 1999.. ትዳር የመሠረተች ቢሆንም ልጆች አቅፈው ለመሳም አምላክ አልፈቀደላቸውም፡፡
 


    

  ሰብለ ተፈራ መንፈሳዊ ህይወቷ ቤተ ክስቲያናትን በማገልግል ትታወቃለች፡፡ ጳጉሜ 5 /2007.. ቱሉ ዲምቱ - አቃቂ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመገኘት የእራሷን ግጥም ‹‹የመዳን ቀን ዛሬ ነው›› እና የገጣሚ ኤፍሬም ስዩምን ‹‹የጅራፍ ንቅሳት›› የተሰኙ ግጥሞችን አቅርባለች፡፡ የአርቲት ሰብለ ተፈራ የቀብር ሥነ ሥርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል  ሰኞ መስከረም 3 ቀን 2008. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ወዳጅ ዘመዶቿና አድናቂዎቿ በተገኙበት ይፈጸማል፡፡ የአርቲስት ሰብለ ተፈራ ባለቤት የሆነው አቶ ሞገስ ተስፋዬ ፍርድ ቤት ይቀርባል ፡፡ በፓሊስ ታጅቦም የቀብር ስነ ስርዓቷ ላይ መንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ይገኛል፡፡ ባለቤቷ ሞገስ ተስፋዬ አደጋው ሙዚቃ ለመቀየር ጎንበስ ሲል እንደተከሰተ ተናግሯል:: 

                            ምንጭ ፡-   Getahun Abebe OrMulatu