Saturday, November 29, 2014

ፎርብስ የ2014 የዓለማችን ቢሊየነሮች እነኚህ ናቸው ብሎ ይፋ አድርጓል

    
     በትውልድ ኢትዮጵያዊና በዜግነት ሳውዲ አረቢያዊ የሆኑት ሼክ መሀመድ አሊ አላሙዲ 13. 6 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከዓለም 80 ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የዓለማችን ቁጥር አንድ ቢሊየነርነትን ከአራት ዓመታት በኋላ አሜሪካዊው ቢል ጌትስ 82 . 4 ቢሊየን ዶላር ባለቤት በመሆን መልሶ ተረክቦታል።

   ከቢል ጌትስ በመቀጠልም የሜክሲኮ ዜግነት ያላቸው ካርሎስ ስሊም 79 .9 ቢሊየን ዶላር በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። አሜሪካዊው ዊገን ቡፌት 72 .7 ቢሊየን ዶላር ሶስተኛ ናቸው። የፌስቡክ መስራችና ባለቤት የሆነው ማርክ ዙከርበርግ 34 . 2 ቢሊየን ዶላር ከዓለም 14 ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ከወጣቶች ደግሞ በሃብት መጠኑ 1 ሆኗል። 
  ናይጄሪያዊው ባለፀጋ አሊኮ ዳንጎቴ 20 ነጥብ 3 ቢሊዮን የአሜሪካምን ዶላር ሀብት ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም ደግሞ 37 ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በአጠቃላይም ፎረብስ 1 ሺህ 645 ቢሊየነሮችን ዝርዝር ይፋ ያደረገ ሲሆን ከነዚህም 268 አዲስ መሆናቸው ታውቋል።  
                                                                                                                            ምንጭ ፡- ኤፍ.ቢ.ሲ

Thursday, November 27, 2014

ለጥምቀት ጎንደር እንገናኝ …………!!!

                                          
ጥር ላይ ጎንደር ደመቅመቅ ትላለች ምክንያቱም ጥምቀት በጎንደር በልዩ ሁኔታ ይከበራልና፡፡ በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ጎብኚዎችም ጥምቀትን በአፄ ፋሲል መዋኛ ማሳለፍን ይመርጣሉ፡፡ ለበዓሉ ወደ ጎንደር ጎራ ካሉ በበዓሉ ላይ ታድመው እግረ መንገድዎን በጎንደር ከተማም ሆነ በአቅራቢዋ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን ጎብኝተው ይመለሳሉ፡፡


   የጎንደር ከተማ ዋነኛ የቱሪስት መስህብ ሀብቶች የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ነገስታት ያሰሯቸው አብያተ መንግስታት እና አብያተ ክርስቲያናት ናቸው፡፡ አብያተ መንግስታቱ በከተማዋ መሀል በሚገኘው ከፍተኛ ስፍራ ላይ “የአፄ ፋሲል ግቢ” ተብሎ በሚታወቀው ሰፊ ቅጥር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የግቢው ስፋት 70,000 ካሬ ሜትር ይሆናል፡፡ ከ17ኛው እስከ 18ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩ ነገስታት አብያተ መንግስታት እና ሌሎች በርካታ የህንፃ ፍርስራሾችን ይዞ ይገኛል፡፡ እነሱም፡-
1.  አፄ ፋሲል /ዓለም ሰገድ/ 1623 - 1659  የፋሲል ቤተ መንግስት/የፋሲል ግንብን/ አሰርተዋል፡፡
2.  ዮሀንስ 1ኛ /አእላፍ ሰገድ/ 1659 - 1674 ባለ ፎቅ የሆነ የቤተ መፅሀፍ አዳራሽ አሰርተዋል፡፡
3.  እያሱ 1ኛ /አድያም ሰገድ/ 1674 - 1698  የእያሱ 1ኛ ቤተ መንግስትን ››
4.  ዳዊት 3ኛ / አድባር ሰገድ/ 1708 -1713  የመዝሙር አዳራሽ ››   ››
5.  አፄ ባካፋ / መሲህ ሰገድ/  1713 - 1722  የንጉስ ባካፋ ቤተ መንግስት ››
6.  እያሱ 2ኛ / ብርሃን ሰገድ/  1722 - 1749  የእያሱ ሁለተኛ ቤተ መንግሰት ››
7.  እቴጌ ምንትዋብ / የንጉስ ባካፋ ባለቤት/ 1730 - 1755 የንግሰት ምንትዋብ ቤተ መንግሰት / ትልቅ አዳራሽ ቤት/ ያሰሩት ይጠቀሳል፡፡
   
  አብያተ መንግሰታቱ የተሰሩት ከድንጋይ፣ ከእንጨት እና ከኖራ ሲሆን ድንጋዩም ቀላ ያለና ልስላሴ ያለው የተጠበሰ ሸክላ የመሰለ ነው፡፡ ይገኝ የነበረውም ቁስቋም እና ጅብ ዋሻ ከሚባሉ ስፍራዎች እንደነበር ይነገራል፡፡ 
  በአፄ ፋሲል ግቢ ከሚገኙ ህንፃዎች ትልቁ እና ከሞላ ጎደል በደህና ሁኔታ ላይ የሚገኘው የአፄ ፋሲል ቤተ መንግስት ነው፡፡ 32 ሜትር ርዝመት እና 3 ፎቆች እንዲሁም በርካታ የምድር ውስጥ ክፍሎች አሉት ፡፡ ከመጨረሻ ፎቅ በስተ ደቡብ ምዕራብ ላይ በከበሮ ቅርፅ የተሰራ ክፍልም አለ፡፡የህንፃው አራት መአዘን አናቶች የግማሽ እንቁላል ቅርፅ አላቸው፡፡ በተለምዶ የእንቁላል ግንብ ተብለው ይጠራሉ፡፡ እነዚህ የአፄ ፋሲል ቤተ መንግሰት ግብረ ህንፃዎች ጥቅምት 26, 1979 እ.ኤ.አ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት/ ዩኔስኮ/ በአለም ቅርስነት መዝግቧቸዋል፡፡


   ከአፄ ፋሲል ግቢ ውጪ በተመሳሳይ ዘመን የኪነ ህንፃ ጥበብ የተሰሩ በርካታ ህንፃዎችም  ይገኛሉ፡፡ የአፄ ፋሲል መዋኛ፣ በቁስቋም የሚገኘው የእቴጌ ምንትዋብ ግቢ፣ የራስ ሚካኤል ስሁል ግቢ እና የደብረ ብርሃን ስላሴ ዋነኞቹ ናቸው፡፡

Tuesday, November 25, 2014

“አንተ ጎዳና” እና የድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ የህይወት ጉዞ …

   
  ድምፃዊ እና የዜማ ደራሲ ነው፡፡ ወደ ሙዚቃው ከገባባት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ርዕሰ - ጉዳዮች ዙሪያ በርከት ያሉ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ ሁለት ያህል አልበሞችም አሉት በግሉ ማለት ነው፡፡ ከግርማ ይፍራሸዋ ጋር የሰሩትም “መለያ ቀለሜ” የተሰኘ አልበም አለው፡፡ ሙዚቃን የጀመረው በእንግሊዘኛ ዘፈኖች ነው፡፡ “ሳይሽ እሳሳለሁ” ፣ “ውበትን ፍለጋ” ፣ ከዘሪቱ ከበደ ጋር የተጫወተው “ታምሪያለሽ” እና “ትዝታ” ከሰራቸው ነጠላ ዜማዎች  መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ አርቲስት ሚካኤል በላይነህ፡፡ 

   ለቤተሰቦቹ 4ኛ እና የመጨረሻ ልጅ የሆነው ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ ትውልዱ አራት ኪሎ ሲሆን እድገቱ ደግሞ ኮተቤ አካባቢ ነው፡፡ በደጃዝማች ወንድራድ ፣ በገዳመ -ሴታውያን እና በጥቁር አንበሳ ት/ቤቶች ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ተምሯል፡፡ ከባህር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ዩኒቨርስቲ በኢንዱስትሪያል ኤለክትሪክሲቲ በአድቫንስ ዲፕሎማ ተመርቋል፡፡ ከዚያም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በፖለቲካል ሳይንስ እና አለም አቅፍ ግንኙነት ዲግሪውን አግኝቷል፡፡ በያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት ፒያኖ ተምሯል፡፡ ከዚህም ባሻገር ኦን ላይን የተለያዩ ስልጠናዎችን በመውሰድ የሙዚቃ ክህሎቱን እያዳበረ ይገኛል፡፡

በኢንዱስትሪያል ኤሌክትሪክሲቲ ከተመረቀ በኋላም በከተማ ፕላን ለአራት አመት ያህል አገልግሏል፡፡ በወቅቱ ይከፈለው የነበረው 420 ብር ስላላረካው ወደ ሌሎች ሙያዎች እና ሙዚቃ ተሸጋገረ፡፡ ከዚያም ቦሌ መንገድ “ፐርፕል” የሚባል ካፌ ከሌሎች ሰዎች ጋር ከፍቶ ይሰራም ነበር፡፡ ካፌው ተወዳጅ በመሆኑ በርካታ ሰዎች ይስተናገዱበት ነበር አርቲስቶችን ጨምሮ፡፡ ለአብነትም ላፎንቴኖች ፣ ጆኒ ራጋ ፣ ኤልያስ መልካ እና ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ይጠቀሳሉ፡፡

     አርቲስት ሚካኤል በላይነህ የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን በማንሳት በዛ ያሉ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ ለአፍሪካ ህብረት በተሰራ ዘፈን ላይ በድምፅ ተሳትፏል፡፡ በተለይ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ  ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ላይ በርከት ያሉ ዜማዎችን ደርሷል፡፡ በድምፅም ተሳትፏል፡፡ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል፡- “ማለባበስ ይቅር - ማወቅ ነው መሰልጠን” ፣ “መላ መላ” ፣ “መታመን ማመን ነው ” ፣ “ኦሮሚኛ - መሌ ሀራ” እና ሌሎች አራት ያህል ዜማዎችን ሰርቷል፡፡
   
  በቅርቡም ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ /አባይ/ “ከፍ እንበል” የተሰኘውን ዘፈን ዜማ ደርሷል፡፡ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በተያያዘም ከዘሪቱ ከበደ ጋር በመሆን “ኢትዮጵያ አረንጓዴ” የሚል ስራም ሰርቷል፡፡ በተጨማሪም ለስኳር ህሙማን የተሰራ “ስኳርን አየሁት” የሚል ዜማም አለው፡፡ ይህንን ዘፈን አብነት አጎናፍር ፣ ግርማ ተፈራ ፣ ሀይልዬ ታደሰ እና ጥላሁን ገሰሰ ተጫውተውታል፡፡


     በአንድ ወቅት በሽራተን አዲስ በተደረገ ዝግጅት ላይ ከእነ ጥላሁን ገሰሰ ፣ መሀሙድ አህመድ ፣ ምኒሊክ ወስናቸው እና ሀመልማል አባተ ጋር ስራውን አቅርቧል፡፡ በጊዜው ከመዲና ባንድ ጋር ከጥላሁን ገሰሰ ቀጥሎ በሁለተኛነት ስራዎቹን ተጫውቷል፡፡ ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ ለራሱም ሆነ ለሌሎች አርቲስቶች በርከት ያሉ የዜማ ድርሰቶችን ሰርቷል፡፡ “አንተ ጎዳና” ከተሰኘው አልበሙ ከ11 ስራዎቹ 9ኙ የእሱ የዜማ ድርሰቶች ናቸው፡፡ “ናፍቆት እና ፍቅር” ከሚለው አዲሱ አልበም ደግሞ ከ13ቱ 11 ያህሉን ዜማ የሰራው እራሱ ነው፡፡ በቀጣይም ለሌላ አልበም ስራ እየተዘጋጀ ነው፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን እናንተ አክሉበት…….!!!




Tuesday, November 18, 2014

በሳምንቱ መጨረሻ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ድል ቀንቷቸዋል



 ስፔን፡- 2014/2015 የአገር አቋራጭ ውድድር መክፈቻ በቀዝቃዛ እና በነፋሻ ማለዳ ኢማና መርጊያ 4ተኛ ተከታታይ ድሉን ሲያስመዘግብ በላይነሽ ኦልጅራ በሴቶች አሸናፊ ሆናለች፡፡ በ2014/2015 የዓለም አገር አቋራጭ በስፔን ቡርጎስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በውድድሩ ሦስት ተከታታይ ወርቅ ማስመዝገብ የቻለው ኢማነ መርጊያ አሸንፏል፡፡


  ኢማነ መርጊያ ከሌላኛው ኢትዮጵያዊ ኢድሪስ ሙክታር ጋር ያደረገው ከፍተኛ የማሸነፍ ትግል የብዙዎችን ቀልብ መሳብ የቻለ ሲሆን ይማነ 9.8 ኪሎ ሜትሩን ለማጠናቀቅ 27 ደቂቃ 39 ሰከንድ ወስዶበታል፡፡ በውድድሩ በላይነሽ ኦልጅራም በሴቶቹ ባለድል መሆን ችላለች፡፡



 ኔዘርላንድ፡- በኔዘርላንድ በተደረገ 15 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አንደኛ እስከ አራተኛ ወጡ፣ አበራ ኩማ 4218 ቀዳሚ ሲሆን ይገረም ደመላሽ 4226 ሁለተኛ የኔው አላምረው 4230 ሶስተኛ ወጥቶአል፡፡

ቱርክ፡- በኢስታንቡል 36ተኛው ኢስታንቡል ማራቶን አማን ጎበና 22846 አሸናፊ ሆናለች፣ ሶሎሜ ጌትነት ሁለተኛ ወጥታለች፡፡ በወንዶቹ ሞሮኮዋዊውን ሀሊድ ቻኒ ተከትሎ ኢትዮጵያዊው ገቦ ቡርቃ 21223 ሁለተኛ ወጥቶአል፣ ዘንድሮ ያደረጋቸውን ሶስቱንም ውድድሮች ማሸነፍ የቻለው ገቦ የመጀመሪያ ሽንፈቱ ሆኖአል፡፡
 
ፈረንሳይ፡- 18ተኛው ቦሎኝ ግማሽ ማራቶን ይታያል አጥናፉ ኣሸናፊ ሲሆን ይሁንልኝ አዳነ ሶስተኛ ወጥቶአል፣ በሴቶች በቀለች በጻጻ ቀዳሚ ሆናለች፡፡

ስዊዝ፡- ኢትዮጵያዊው ኢፋ ባላድ 8ኪሎ ሜትር የጎዳና ውድድር አሸናፊ ሲሆን በሴቶች 6 ኪሎ ሜትር ለካናዳ የምትሮጠው አስቴር ደምሴ ሁለተኛ ወጥታለች፡፡

ጃፓን፡- ዮኮሀማ የሴቶች ማራቶን ቶኦሚ ታናካ ቀዳሚ ስትሆን ኢትዮጵያዊቷ ቲኪ ገላና 22913 ስድስተኛ ወጥታለች፡፡

Sunday, November 9, 2014

Abuna Yemata Guh Church


Abuna Yemata Guh has been on the clifftop on Northern Ethiopia since 5th century ADA leap of faith! Ethiopia's 'church in the sky' is perched on a 2,500ft cliff... with a wall of rock devotees must climb barefoot It is arguably the most inaccessible place of worship on earth, perched on top of a vertical spire of rock, with sheer, 650 feet drops on all sides.


   Abuna Yemata Guh, the church carved into the rock at the top of the cliff, is named for a shadowy fifth-century saint. Abuna means "priest," and Yemata is one of nine who is believed to have fled persecution elsewhere in the Roman Empire. The Ethiopians call these nine foreigners Syrian, because they were white. Guh, means "sunrise." Ethiopians say that from the summit you can see where the world begins.I've made much easier climbs than this one wearing a harness. If the monk, my driver-cum-guide Yonas, and I were climbing in the United States, we would be clipped to each other and to the rock.


    To visit requires a six-metre climb up sheer wall of rock with no ropes and crossing narrow ledges with 200m drops . The churches are as rewarding to visit as they are (often) difficult to reach. Abuna Yemata Guh is a particular highlight, although not recommended for those with a fear of heights. The tourist office in Wukro can help to arrange guides and transport. Mekele is part of the famous Ethiopia Historical Circuit.

Thursday, November 6, 2014

ተንቀሳቃሹ ቤተ- መዘክር ……. አርቲስት ጌታቸው ደባልቄ


     በብዙዎች ዘንድ ተንቀሳቃሽ ቤተ መዘክር ተብለው ይታወቃሉ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ትያትር ህንፃው ታንፆ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ስማቸው አብሮ ይጠራል፡፡ አንዳንድ ጓደኞቻቸውም ሆኑ በቅርብ የሚያውቋቸው ስለ ብሄራዊ ትያትር መረጃ ሲፈልጉ ወደ እሳቸው መሄድን ይመርጣሉ፡፡ እኚህ ሰው ደራሲ ብቻ ሳይሆኑ የመድረክ ተዋናይ እና የትያትር አዘጋጅም ናቸው፡፡ አርቲስት ጌታቸው ደባልቄ፡፡
 
  አርቲስት ጌታቸው ደባልቄ ከአዲስ አበባ 50 ያህል ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው አዲስ አለም ሚያዚያ 20/1928 ዓ.ም ነው የተወለዱት፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በትውልድ ከተማቸው በአዲስ አለም እስከ 6ኛ ከተማሩ በኋላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለመከታተልም ወደ አዲስ አበባ መጡ፡፡

  በአዲስ አበባም ልባቸው ወደ ሙዚቃው እና ትያትሩ በመሳቡ ትምህርታቸውን ብዙም ሳይገፉ አቋረጡ፡፡ በተስፋ ኮኮብ ት/ቤትም ከአንድ ሴሚስተር በላይ እንዳልገፉም ይነገራል፡፡


 ገና በወጣትነት እድሜያቸው በ1944ዓ.ም በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የትያትር እና ሙዚቃ ማስፋፊያ ክፍል ውስጥ በመግባት ስራን አሀዱ አሉ፡፡ከዚያም ከተወሰኑ አመታት በኋላ ከማዘጋጃ ቤት ወደ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ትያትር በመዛወር የህይወታቸውን ብዙውን ምዕራፍ በትያትር እና በሙዚቃው ዘርፍ አሳልፈዋል፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ የትያትር ተመልካቹ ቁጥር በጣም ትንሽ ነበር፡፡ እነዚህን ተመልካቾች ለመሳብም መንገድ ዳር በመውጣት ዘፈን በመዝፈን እና ትያትሩን በማስተዋወቅ ሰው ሲገባ ልብሳቸውን ቀይረው ይሰሩ እንደነበርም ያወሳሉ፡፡


   በ1946ዓ.ም ጀምሮ ነው የራሳቸውን የትያትር ድርሰት መፃፍ የጀመሩት፡፡ አርቲስት ጌታቸው ደባልቄ በትያትሩ ዘርፍ ባሳለፏቸው 50 ዓመታት 52 ትያትሮችን ተጫውተዋል፤ 15 ያህል ተውኔቶችን አዘጋጅተዋል፤ 10 ያህል ድርሰቶችን ደግሞ ራሳቸው ደርሰው ለመድረክ አብቅተዋል፡፡ ከተወኑባቸው ትያትሮች መካከል ለአብነት ጥቂቶቹን አናንሳ ፡-

“ዳዊት እና ኦሪዮን፣ ጎንደሬው ገብረማሪያም፣ የሺ /የፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ድርሰት ነው/ ፣ የፌዝ ዶክተር /ዶክተር ሆነው የተወኑበት/ ፣ አወናባጅ ደብተራ / ደብተራ ሆነው የተጫወቱበት/ ፣ በልግ / ወፈፌው ሰዓሊ/ ፣ የከርሞ ሰው / 3 ሆነው የተወኑበት ሲሆን ፡- አውላቸው ደጀኔ፣ ተስፋዬ ሳህሉ እና ጌታቸው ደባቄ ተሳትፈውበታል/ ፣ ዋናው ተቆጣጣሪ / ከንቲባ ሆነው/ ፣ ሀሁ በ6ወር ፣ ቴዎድሮስ ፣ ስነ - ስቅለት፣ ኦቴሎ ፣ አምሌት ፣ የአዛውንቶች ክበብ ፣ አፅም በየገፁ ፣ ሀኒባል ፣ ተሀድሶ ፣ ሻጥር በየፈርጁ ፣ በቀይ ካባ ስውር ደባ ፣ የአመፃ ልጆች እና እርጉም ሀዋሪያ” ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡


     አርቲስት ጌታቸው ደባልቄ ከ 1944 - 1946 ዓ.ም ድረስ በማዘጋጃ ቤት በነበራቸው ቆይታ “ድንገተኛ ጥሪ ፣ እድሜ ልክ እስራት እና የፍቅር ጮራ” ትያትሮች ላይ ተውነዋል፡፡ ከላይ ለመጥቀስ የተሞከሩትን ብዙዎቹን በብሄራዊ ትያትር እያሉ የሰሩባቸው ናቸው፡፡ ጡረታ ከወጡ በኋላም “በንጉስ አርማህ” ትያትር ላይ ተውነዋል፡፡እሳቸው ከደረሷቸው ትያትሮች መካከል “በድሉ ዘለቀ” የመጀመሪያ ስራቸው ሲሆን በመዘጋጃ ቤት ነው የታየው፡፡ በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ትያትር ቤት ከታዩት መካከል ደግሞ “የፍቅር ሰንሰለት ፣ ያስቀመጡት ወንደ ላጤ ፣ ደህና ሁኚ አራዳ  እና የሮምነሽ” የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ 


   በሙዚቃው ረገድም በርከት ያሉ ግጥም እና ዜማዎችን ደርሰው ለተለያዩ ድምፃውያን ሰጥተዋል ፡፡ የተወሰኑትን ለማየት እንሞክር፡-
1.  ለ ግርማ ነጋሽ  - / የኔ ሀሳብ ፣ ምነው ተለየሽኝ ፣ እንገናኛለን እና አልበቃኝም ገና/
2.  ለ አባባ ተስፋዬ /ተስፋዬ ሳህሉ/ -  አለም እንዴት ሰነበተች
3.  ለ አስናቀች ወርቁ - / በል ተነሳ ልቤን ጨምሮ 9 ያህል ስራዎችን /
4.  ለ ምኒሊክ ወስናቸው - / አደረች አራዳ ፣ አልማዝዬ አሰብኩሽ /
5.  ለ መኮንን  በቀለ - / ፍቅርን እውር ነው አትበሉ / እንዲሁም
6.  ለ ጠለላ ከበደ - / ሎሚ ተራ ተራ እና ሌሎችንም ደርሰዋል፡፡
  
    ሎሚ ተራ ተራ በሚለው የግጥም ስራቸውም በደርግ ዘመነ መንግስት ለ 4 ዓመት ያህል ታስረዋል፡፡ በእስር ቤት ቆይታቸውም “ደንቆሮ በር” የሚል መፅሀፍ አሳትመዋል፡፡ መፅሀፉ የእስር ቤት ቆይታቸውን የሚያወሳ ሲሆን በጊዜው ያዩትን፣ የታዘቡትን እና አጠቃላይ የእስር ቤቱን ሁኔታ የሚያሳይ ነው፡፡ የደንቆሮ በር መፅሀፍ ከ 60 - 70 ገፆች እንዳሉትም ይናገራሉ፡፡

   በጳጉሜ 5,1953/54ዓ.ም የዘፈን ግጥም ውድድር ነበር፡፡ በዚህ ወቅት አርቲስት ጌታቸው ደባልቄ የኔሀሳብ የሚለውን የዘፈን ግጥም በማቅረብ ይወዳደራሉ፡፡ ተወዳድረውም አንደኛ በመውጣት 25 ብር ተሸልመዋል፡፡ በወቅቱ ለኦርኬስትራው ፣ ለድምፃዊው እንዲሁም ለግጥም እና ዜማ ደራሲው አጠቃላይ የተሰጠው ሽልማት 250 ብር ነበር፡፡ ይህ ሲከፋፈል ነው ለእያንዳንዳቸው 25 ብር የደረሳቸው፡፡

  የአርቲስት አስናቀች ወርቁ እና የ (አባባ) ተስፋዬ ሳህሉ የህይወት ታሪክን የተመለከተ መፅሀፍም ፅፈዋል፡፡ በተጨማሪም የብሄራዊ ትያትርን ታሪክ በተመለከተ እና የዘፈን ግጥሞቻቸውን እየፃፉም እንደሆነ አጫውተውኛል፡፡በቀድሞው ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በአሁኑ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ትያትር እስከ 1966ዓ.ም ድረስ በህዝብ ግንኙነት እና የትያትር ክፍል ሀላፊ እንዲሁም ፕሮግራም እና ፕሮዳክሽንን በተጠባባቂነት በመምራት በልዩ ልዩ ሀላፊነት አገልግለዋል፡፡


   በ1994ዓ.ም የኢትዮጵያ ስነ ጥበባት እና መገናኛ ብዙሃን ሽልማት ድርጅት በተውኔት ዘርፍ “የህይወት ዘመን” ተሸላሚ ናቸው፡፡ በዚህም የወርቅ ሜዳሊያ ፣ የክብር ዲፕሎማ እና የ 20,000 ብር ሽልማትን አግኝተዋል፡፡ አርቲስት ጌታቸው ደባልቄ የሁለት ሴቶች እና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ናቸው፡፡