Sunday, January 26, 2014

ሁዋን ማታ በ37.1 ሚሊዮን ፓውንድ ዩናይትድን ተቀላቀለ


       ሁዋን ማታ ትናንት በማንችስትር ዩናይትድ የማሰልጠኛ ማዕክል ካሪንግተን ሲገኝ በዩናይትድ ተጨዋቾች ደማቅ አቀባብል ተደርጎለታል፡፡ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ወደ ቡድናችን ማካተት ከምንፈልጋቸው ተጨዋቾች የመጀመሪያው እኛን ተቀላቅሏል ሲሉ ሁዋን ማታ በበኩሉ በማንችስትር ለአዲሱ ፈተና ተዘጋጅቻለሁ በማለት ተናግሯል፡፡
          

    ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዲያ ፣ሪዮ ፈርድናንድ እንዲሁም ሮፐን ቫንበርሴ ሁዋን ማታን እንኳን ደህና መጣህ ብለውታል በቲውተር ገጻቸው፡፡ 

     በመጪው ማክሰኞ ዩናይትድ ከካርዲፍ በኦልትራፍርድ በሚያድርጕት ጨዋታ ሁዋን ማታ የመጀመሪያ የዩናይትድ ግዳጁን ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

      ደካማ የውድድር ዓመትን እያሰለፈ የሚገኘው ማንችስትር ዩናይትድ የክለቡን የተጨዋች ግዥ ክብረ ወሰን በሰበረ የዝውውር ዋጋ በ37.1 ሚሊዮን ፓውንድ ሁዋን ማታን ከቸልሲ አስፈረመ፡፡

No comments:

Post a Comment