Saturday, October 19, 2013

ድሮግባ የወርቅ ጫማ ተሸላሚ ሆነ


 የ35 ዓመቱ ኮቱዲቭዋራዊ የጋላታሳራይ አጥቂ ዲደር ድሮግባ የ2013 ከ28 ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸውና እስካሁንም አየተጫወቱ የሚገኙ ኮከብ ተጨዋቾች ምርጫን አሸነፈ፡፡ 

ድሮግባ ይህን ሽልማት ሲያሸንፍ የመጀመሪያው አፍሪካዊ አድርጎታል፡፡በእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ከተጫወቱ ተጨዋቾች ደግሞ ከርያን ጊግስ ቀጥሎ የወርቅ ጫማ ሽልማቱን በማገኘት ሁለተኛው ነው፡፡
 በውድድሩ ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ሳሙኤል ኢቶ፣ ዴቪድ ትርስጌ፣ ላምፓርድ፣ ኢኔስታ፣ ፔርሎ፣ ካሲያስ፣ ቤካም እንዲሁም ሚርስላቭ ክሎስ ተካተው ነበር፡፡ ዘላታን ኢብራሄሞቪች የባለፈው ዓመት የወርቅ ጫማ አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል፡፡
                                                                              ምንጭ፡ስታር አፍሪካ ዶት ኮም

No comments:

Post a Comment