Thursday, December 5, 2013

ከንቲባ ድሪባ በመርካቶ በእሳት አደጋ የተጎዳውን ስፍራ ጎበኙ

   የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ  ትናንት ከሰዓት  8:30 ላይ በመርካቶ በተለምዶ ጆንያ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በእሳት አደጋ የተጎዳውን ስፍራ ጎበኙ። ከንቲባው እንዲሁም የአስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ስለአደጋው ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን በአደጋው ንብረታቸው የወደመባቸውን ተጎጂዎች ጎብኝተዋል።


    አቶ ድሪባ  የከተማ አስተዳደሩ በትናንትናው እለት በደረሰው የእሳት ቃጠሎ አደጋ በእጅጉ ያዘኑ  መሆኑን ጠቅሰው ተጎጂዎቹ በፍጥነት ወደ ስራቸው የሚመለሱበት ሁኔታ ያመቻቻል ብለዋል። የአደጋው መንስኤም ተጣርቶ በአፋጣኝ ይፋ እንደሚሆንም ተናግረዋል። በተያያዘ ዜና  በአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በአደጋው 10 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። እንደ አቶ ንጋቱ እነዚህ  ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ተክለሃይማኖት ሆስቲታልን ጨምሮ በተለያዩ የህክምና ተቋማት የህክምና እርዳታ ተደርጎላቸዋል።

   እሳቱን ለማጥፋት 12 መኪኖች በስራ ላይ የተሳተፉ ሲሆን   ሌሎች የውሃ ማመላለሻ  ቦቴዎችም ውሃ በማቅረቡ ተሳትፈዋል።
ለአደጋው መባባስ የቤቶቹ አሰራርና በውስጣቸው ያሉ ተቀጣጣይ ነገሮች በምክንያትነት የተጠቀሱ ሲሆን በንብረት ላይ የደረሰውን  አደጋ ከአሁን በኋላ የሚታወቅ መሆኑን አቶ ንጋቱ ተናግረዋል። ትናንት 9:14 ሲል የስልክ ጥሪ ደረሰን ያሉት አቶ ንጋቱ አደጋው በደረሰበት አቅራቢያ ያሉት የአዲስ ከተማና የአራዳ ጣቢያ ኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የእሳት አደጋ  ሰራተኞች ጋር በመተባበር እሳቱን  ምሽት 3 ሰዓት ሲሆን በቁጥጥር ስር አውለውታል።
 
በአደጋው በሁለት መደዳዎች በሚገኙ ህንፃዎች ውስጥ የሚገኙ የምገብ ዘይቶች፣ የሽቶዎች እና  የጆንያ መጋዘኖችና  ሱቆች ሙሉ በሙሉ  ወድመዋል፡፡
                                                                                ምንጭ፡-  FBC

No comments:

Post a Comment