Wednesday, March 10, 2021

ድምፃዊት እና ተዋናይት ዘቢባ ግርማ - ገራገር …!!!


ገራገር  ያማል ቅኔው አዲስ ፍቅር የተሰኙት ዘፈኖች ከተወዳጅ ስራዎቿ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ ለማን ብዬ ፍቅር ይብዛ አበባየሆ ጣይቱ እና ሌሎች ሙዚቃዎችን በግል እና በጋራ ተጫውታለች፡፡ በተለይ ገራገር በአንድ ቀን ውስጥ 500,000 በላይ የዩቲዩብ እይታ በማግኘት ሪከርድም ይዞ ነበር፡፡ ከድምፃዊነቷ ባሻገርም የእኛዎቹን በመቀላቀል በሬዲዮ ድራማ እሙዬን ገፀ ባህሪ በኋላም ምን ልታዘዝ የተሰኘ የቴሌቭዥን ድራማ ላይ ደግሞ የንጉስ ነሽን ገፀ ባህሪ ወክላ በመጨዋት ተወዳጅነትን አትርፋለች፤ ድምፃዊት እና ተዋናይ ዘቢባ ግርማ፡፡


ከትምህርት ቤት የጀመረው የሙዚቃ ፍላጎት እና ተስጥኦ በብዙ ውጣውረዶች ውስጥ አልፋ አሁን ላለችበት ደረጃ ደርሳለች፡፡ ተማሪ እያለችም በት/ቤቶች መካከል በሚደረግ የሙዚቃ ውድድር በመሳተፍ አንደኛ አንደኛ እየወጣች የተለያዩ ሽልማቶችን አግኝታለች፡፡ የሸገር ሬዲዮ የድምፃውያን ውድድር ላይ 3 ወጥታ ብታሸንፍም በኢትዮጵያ አይዶል ውድድር ግን 3 ዙር መሻገር አልቻለችም ነበር፡፡

ከክቡር / ተስፋዬ አበበ የጥበብ ማዕከል የኛዎቹ የተመረጠችው ዘቢባ በቡድኑ ውስጥ 5ሴት እና 1 ወንድ ሆነው የተለያ የሙዚቃ የሬዲዮ ድራማ እና የሙዚቃ ኮንሰርቶችን በመስራት በጋራ 8 አመታት አብረው ዘልቀዋል፡፡ በዚህ ቆያታቸውም 40 ያህል ሙዚቃዎችን ሰርተዋል፡፡ ከየኛዎቹ ወደ እንደኛ የሙዚቃ ቡድን ቢመጡም አሁን ላይ ከቡድን ስራቸው ይበልጥ በየግል በሚሰሯቸው ስራዎች ውጤታማ እየሆኑ ነው፡፡


በስራዎቿ ተወዳጅነትን ያተረፈችው ድምፃዊት እና ተዋናይ ዘቢባ ግርማ በሀገር ውስጥ እና በውጪ የተለያ አካባቢዎች ስራዎቿን አቅርባለች፣ እያቀረበችም ነው፡፡ በቀጣይም በአልበም ለመምጣት እንዳሰበች ጠቆም አድርጋናለች፡፡ ዘቢብ ጅማሬሽ ጥሩ ነውና ፍፃሜሽም እንዲያምር መልካሙን ሁል እንመኝልሻለን፡፡