Thursday, December 19, 2013

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር ሆነው ተሾሙ


          አስቸኳይ  ስብሰባውን ከትናንት ምሽት ጀምሮ በባህር ዳር ያካሄደው የአማራ  ክልል ምክር ቤት የክልሉን ርእሰ መስተዳድር ሾሟል። ምክር ቤት ለስምንት ዓመት ተኩል ክልሉን ያገለገሉት አቶ አያሌው ጎበዜን በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተክቷል።

     አቶ ገዱ ክልሉን በምክትል ርእሰ መስተዳድርነትና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ለምክር ቤቱ የስንብት  ንግግር ያቀረቡት አቶ አያሌው  ጎበዜ የክልሉ  መንግስትና ህዝብ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና  አቅርበዋል። አቶ አያሌው ለአዲሱ ርዕሰ መስተዳድርም መልካም  የስራ  ዘመንን ተመኝተዋል።

     የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/  የድርጅት ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ፈንታ  ደጀን  እንደተናገሩት፥ አቶ አያሌው ጎበዜ ባቀረቡት ጥያቄ  እና  የድርጅቱን የመተካካት መርህ  መሰረት በማድረግ ወደ ሌላ  ሀላፊነት ተዘዋውረዋል። አቶ ብናልፍ አንዱዓለምም  የክልሉ ምክትል  ርእሰ መስተዳደር ሆነዋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢንዱስትሪና  ከተማ ልማት ቢሮ ሀላፊ  በመሆን ደግሞ ዶክተር አምባቸው መኮንን ተሹመዋል።

       የሙያና ቴክኒክ ኢንተርፕራይዞች፣ የባህልና ቱሪዝም፣ የውሃ እንዲሁም የአከባቢ ጥበቃና መሬት አስተዳደር ቢሮዎች አዳዲስ  ሀላፊዎችም  በምክር ቤቱ  ተሹመዋል።
                                                                                      ምንጭ ፡ -  ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት

No comments:

Post a Comment