Thursday, December 12, 2013

የዳግማዊአፄ ምኒልክ ህልፈት - /ታህሳስ 3/2006ዓ.ም./


   
    100ኛዓመትበዛሬው እለት አጽማቸው ባረፈበት አራትኪሎ በሚገኘው በዓታ ታዕካ ነገስት ገዳም ቤተክርስቲያን ይከበራል፡፡ በስነ ስርዓቱ ላይ የንጉሰ ነገስቱ ስራናህይወት ይዘከራል፡፡ 
    
   ዳግማዊ አፄ ኒልክ በ1888ዓ.ም የመላው ኢትዮጵያን ህዝብ በማስተባበር ወራሪውን የጣልያን ጦር አድዋ ላይ ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡ ይህም ኢትዮጵያን በቅኝግዛት ያልተያዘች ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ያደርጋታል ፡፡ 

   ዳግማዊ አፄ ኒልክ ዕለተ - ቅዳሜ ነሐሴ 12/ 1836 .ም በሰሜን ሸዋ አንጎለላ ኪዳነምህረት የተወለዱ ሲሆን በ1881 ንጉሰ - ነገስት በመሆን ዘውድ ደፍተዋል፡፡
  
    አፄ ምኒልክ ሕመም ጸንቶባቸው ነበርና ታኅሳስ 3 ቀን 1906 .. በዕለተ ዓርብ ሞቱ፡፡ ወዲያው እንደሞቱ የግቢ ሥራ ቤቶች የልቅሶ ድምፅ አሰሙ፡፡ ነገር ግን የልጅ ኢያሱ ባለሟሎች አገር እንዳይሸበር ሰግተው በቶሎ ዝም አሰኟቸው፡፡ አቤቶ ኢያሱ በዚያ ዕለት ያደሩት ፍልውሃ በሚባል የመታጠቢያ ቤታቸው ነበር፡፡ እዚያው እንዳሉ ማለዳ የአባታቸውን የአምኒልክን መሞት ሲሰሙ ደንግጠው ወደቤታቸው ወጥተው ተቀመጡ፡፡ ሆኖም ሀገር እንዳይሸበር በማለት ኀዘናቸውን በይፋ አላሳዩም፡፡

     እንዲያውም አንዳች ኀዘን አለመኖሩን ለማስመሰልና ለማሳመን ሲሉ በማግሥቱ ቅዳሜ ወደ ጃን ሜዳ ወጥተው ከአሽከሮቻቸው ጋር በፈረስ ጉግስ ሲጫወቱ ዋሉ፡፡ ይህም ለሀገር ጸጥታ ሲባል አማካሪዎች ያቀረቡላቸው ዘዴ መሆኑ አይጠረጠርም፡፡ ስለዚህ የአምኒልክ ሞት ሚስጥር ሆኖ ተደበቀ፡፡ የአምኒልክን አስክሬን አሽከሮቻቸው እንደ ነገሥታት ማዕረግ አምሮ በተሠራ በብረት ሣጥን አድርገው በቤተመንግስቱ ግቢ ውስጥ ባለችው በሥዕል ቤት ኪዳነ - ምህረት ቤተክርስቲያን በክብር አስቀመጡት፡፡
    
  ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱና ልጃቸው ወይዘሮ ዘውዲቱ በሳጥኑ አጠገብ ሆነው መሪር ልቅሶ ያለቅሱ ነበር፡፡  ከዚህ በኋላ አምኒልክ በሕይወት አሉ እየተባለና እየተወራ እስከ ሰገሌ ዘመቻ ድረስ ሁለት ዓመት ከአሥር ወር ተደበቀ፡፡ የመንግሥቱ ሥራም በስማቸው ይካሄድ ነበር፡፡ አፄ ምኒሊክ በስድሳ ዘጠኝ ዓመት ከአራት ወራቸው ነበር ከዚህ አለም በሞት የተለዩት፡፡


   ምንጭ፡-     (መርስዔኀዘንወልደቂርቆስ - ትዝታዬ - ስለራሴየማስታውሰው 1891-1923)

No comments:

Post a Comment