Thursday, January 28, 2021

ያልተዘመረላት የጥበብ ሰው ... ሁለገቧ ባለሙያ አርቲስት አስታውሺኝ በነጋ፡፡

 

30 በላይ ትያትሮች ላይ ሰርታለች፡፡ በዝግጅት - 14 በድርሰት - 7 በቀሪዎቹ ላይ ደግሞ በትወና የሰራች ሲሆን በብዛት በህፃናት ትያትሮች ላይ ባላት ተሳትፎ ትታወቃለች፡፡ ከትያትሩ ባሻገርም ልዩ ልዩ ፊልሞችን የቴሌቭዥን ፕሮግራሞችን እና የሬዲዮ ድራማዎችን ለአድማጭ ተመልካቾች አድርሳለች፡፡ ህፃናት እና ወጣቶችንም የትያትር ሙያ - (ጀርመን ስኩል) ታስተምራለች ታሰለጥናለች ሁለገቧ የጥበብ ባለሙያ አስታውሺኝ በነጋ፡፡

በሀገር ፍቅር  በህፃናት እና ወጣቶች ፣ ሜጋ ኪነ ጥበባት ብሄራዊ ትያትር እና አሁን እየሰራች ያለችበት የአ. ትያትር እና ባህል አዳራሽ(ማዘጋጃ ቤት) ልዩ ልዩ ትያትሮችን ሰርታለች፡፡ ለአብነትም :- 

 1. ሀገር ፍቅር ትያትር ቤት - (ማን ለማን አይዳ ያልተቋጨው እና ምዕራፍ አራት...)

2. ሜጋ ኪነ ጥበብ - (አብሮ አደግ እና ይግባኝ...)

3. ብሄራዊ ትያትር - (13 ወር ፀጋ...)

4. ትያትር እና ባህል አዳራሽ - (እድል 20 ጥቁሩ መናኝ ፍላጎቶቼ እና ነብይ ዤሮ...)

5. ህፃናት እና ወጣቶች (የጠፋችው ልዕልት ብርቅዬዋ ዶሮ ሁለቱ ወንድማማቾች ሰኞ ማክሰኞ አምስቱ ጣቶች የተቀደደው ተራራ ዱዱ ...)

6. እምቢልታ ሲኒማ - (ጠቋሪት የዋሻዋ እመቤት መሃረቤ 1 እና 2 አብቹ ቹቹ ቶፊዬ ሁለቱ አይጦች እና ነይ እርግብ አሞራ...)

በቴሌቭዥን ስራዎችም:- በኢቢሲ - ቤቶች ተከታታይ ድራማ በአዲስ ቲቪ - የተለያዩ ድራማዎች እና ስፖቶች በኢቢኤስ - ልዩ ልዩ የበዓል ስራዎች (4 ቤት እና የኤዞፕ ምድር) አርትስ ቲቪ - አዲስ ድባብ(የልጆች ፕሮግራም) እና አሻም ቲቪ - ንፁህ ነፍሶች (የልጆች ፕሮግራም) የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡

ያልወረደ ሸክምን ጨምሮ 10 የሚጠጉ የሬዲዮ ድራማዎችንም ሰርታለች ፡፡ ጥቁር እና ነጭ 79 አዲስ ሙሽራ - 2 ግልባጭ ፣ሴት እና አሜሪካ ላይ እና ታች እና ካምፓስ ከሰራቻቸው ፊልሞች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ከአ. ዩኒበርስቲ በትያትር ሙያ የመጀመሪያ ዲግሪዋን አግኝታለች፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በህክም ሙያ በነርሲንግ ተመርቃለች፡፡ የሁለት ወንድ ልጆች እናት የሆነችው አርቲስት አስታውሺኝ በነጋ ቀልድ እና ጨዋታ አዋቂ ናት፡፡ ብዙም ስላልተነገረላት እና ስላልተዘመረላት አርቲስት አስታውሺኝ በነጋ ከብዙ በጥቂቱ እኔ ይህንን አካፈልኳችሁ፣ እናንተ ደግሞ በማስፋት እና በማዳበር ተጨማሪ መረጃዎችን ልታጋሩኝ ትችላላችሁ፡፡

ለሁለገቧ ባለሙያ አርቲስት አስታውሺኝ በነጋ እድሜ እና ጤናን እመኛለሁ፤ በሌላ ጊዜ በሌላ እንግዳ እንገናኛለን፡፡ ቸር ይግጠመን !!!