Thursday, December 5, 2013

ኢትዮጵያ የሚሊኒየሮች መፍለቂያ እየሆነች ነው

  ኢትዮጵያ ባለሁለት አሃዝ ኢኮኖሚን ከማስመዝገቧ ባሻገር አሁን ላይ የበርካታ ሚሊየነሮች መፈጠሪያም እየሆነች መምጣቷን ኒው ወርልድ ዌልዝ የተባለው ተቋም ይፋ ባደረገው ጥናት አመለከተ፡፡
    
 ባለፉት ስድስት አመታት በኢትዮጵያ የሚገኙ ሚሊየነሮች ቁጥር በ108 በመቶ እድገት በማሳየት  አንጎላ፣ ታንዛኒያ፣ ዛምቢያ እና ጋናን በማስከተል ቀዳሚዋ ሃገር ሆናለች፡፡
   
   መሰረቱን በደቡብ አፍሪካ እና እንግሊዝ ያደረገው ኒው ወርልድ ዌልዝ የተባለው ተቋም ይፋ ባደረገው ጥናቱ ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሀብትን ያፈሩ ባለሃብቶች ቁጥር በኢትዮጵያ እያደገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

   እንደ ተቋሙ መረጃ ከሆነ በጎርጎሮሳውያኑ 2003 በኢትዮጵያ የነበሩት 1 ሺህ 3 መቶ ሚሊየነሮች በ2013 ወደ 2 ሺህ 7 መቶ አድጓል፡፡ በጥናቱ ላይ እንደተመለከተው ባለፉት ስድስት አመታት በኢትዮጵያ የሚሊኒየሮች ቁጥር እያደገ ቢሆንም በአንጻሩ ደግሞ ባደጉት ሃገራት ያለው የሚሊኒየሮች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል፡፡

    ደቡብ አፍሪካ  በጎርጎሮሳውያኑ 2013 48 ሺህ 7 መቶ ሚሊየነሮችን በመያዝ ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ስትሆን ግብጽ በ22 ሺህ 8 መቶ እንዲሁም ናይጄሪያ 15 ሺህ 7 መቶ ሚሊየነሮችን በመያዝ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡ በሚቀጥሉት አመታት ማለትም እስከ  2030 ሚሊየነሮች በብዛት የሚፈጠሩባቸው ሀገራት  ትንበያ ደግሞ ከአፍሪካ ኮትድቯር፣ዛምቢያ፣ ጋና እና ኢትዮጵያ በደረጃ ተቀምጧል፡፡

ተ.ቁ
ሐገር
ሚሊየነሮች (2007 በጎ.)
ሚሊየነሮች (2013 በጎ.)
ዕድገት
1
ኢትዮጵያ
1,300
2,700
108%
2
አንጎላ
3,800
6,400
68%
3
ታንዛኒያ
3,700
5,600
51%
4
ዛምቢያ
600
900
50%
5
ጋና
1,600
2,400
50%
6
ናይጄሪያ
10,900
15,700
44%
7
አልጀሪያ
2,900
4,100
41%
8
ኮቲዲቯር
1,600
2,100
31%
9
ሞሮኮ
3,900
4,900
26%
10
ኬንያ
6,700
8,300
24%
























በአፍሪካ የሚሊየነሮች ቁጥር ዕድገት በሐገራት የሚያሳየው የጥናቱ  ሰንጠረዥ (በጎርጎሮሳውያኑ 2007– 2013)
                                                  ምንጭ፣ ቢዝነስ ስቲች

No comments:

Post a Comment