Friday, December 13, 2013

4 ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያለው የፈረስ ቅሬተ አካል በኢትዮጵያ ተገኘ


በኢትዮጵያ የ4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያለው የፈረስ ዝርያ ቅሬተ አካል ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች አስታወቁ፡፡

 ዩራይጋናቶሂፐስ ዎልደገብሪየሊ የሚል ሣይንሳዊ ስም የተሰጠው ይህ የፈረስ ቅሬተ አካል በኢትዮጵያ አፋር ክልል ጎና በሚባለው አካባቢ ነው የተገኘው፡፡ በዚህ አካባቢ የተገኘው የፈረስ ቅሬተ አካል የሠው ልጅ ቅድመ ዘር የሆነችው አርዲ እና ሌሎችም ምን አይነት እንስሳትን ይጠቀሙ እንደነበር ለሚደረገው ጥናት አጋዥ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

   ተመራማሪዎቹ እንዳሉት የተገኘው የፈረስ ዝርያ  ባለ ሶስት ሾህና ሲሆን በመጠኑ ከሜዳ አህያ የሚያንስ እና ባለሦስ ጣምራ ሸሆና ሲሆን  ሣር እና ቁጥቋጦዎች በሚበዙበት አካባቢም ይኖር እንደነበር ያመላክታል ብለዋል፡፡

   ስኮት ሲምፕሰን በኬዝ ዌስተርን ሪዘርቭስ የሜዲካል ትምህርት ቤት ውስጥ የሥነ-አካል ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ እናም እሳቸው እንደሚሉት ይህ የፈረስ ዝርያ ቅሬተ አካል መገኘት በፈረስ ቅድመ ዝርያ ላይ ለሚደረገው ጥናት ጉድለትን ከመሙላት ባለፈ በወቅቱ የነበሩት የሠው ልጅ ዝርያ ይጠቀምበት የነበረውን የእንስሳ አይነትም ለመለየት ያግዛል ብለዋል፡፡

   የተገኘው የፈረስ የቅሪተ አካል መዋቅር አሁን ካለው የሜዳ አህያ ጋር ተመሳስሎሽ ያለው ሲሆን  አሯሯጡም ከሜዳ አህያ ጋር የተቀራረበ መሆኑን ነው ተመራማሪዎቹ የተናገሩት።
   
  ተመራማሪዎቹ እንዳሉት የተገኘው የፈረስ ዝርያ ቅሪተ አካል፣ አሁን ካለው የፈረስ ዝርያ ጋር በርካታ ልዩነቶች ያለው በመሆኑ ከ5 ሚሊዮን አመት በፊትም ሆነ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዓመት በኋላ ካሉት የፈረስ ዝርያዎች የተለየ አይነት እንደሆነ ቅድመ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡  
              ምንጭ፦www.redorbit.com

No comments:

Post a Comment