Sunday, December 15, 2013

ወሎ ውስጥ አዲስ የኦፓል ማዕድን ክምችት ተገኘ፡፡

      
 ጎንደር ውስጥ ካለው የኦፓል (የከበረ ድንጋይ) በተጨማሪ በጣሙን የተዋበ ነው የተባለለት የወሎው ኦፓል የብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡ አሁን በቅርቡ ወሎ ውስጥ የተገኘውን የወሎ ኦፓል እንዲቆፍሩ የተፈቀደላቸው የአካባቢው ሰዎች ብቻ ሲሆኑ መንግስት የቁፋሮ መሳሪያ መስጠቱም ተዘግቧል፡፡

   የዓለምን የኦፓል አቅርቦት 97% ያህሉን የምትሸፍነው አውስትራሊያ ስትሆን አሁን ወሎ ውስጥ የተገኘው የወሎው ኦፓል ባለደማቅ ቀለም መሆኑንና ከአውስትራሊያው ኦፓል በተለየ መልኩ ከሰማያዊ ይልቅ ቀይ ቀለም እንደሚበዛበት ተገልጿል፡፡ ከሌሎች ሀገራት በተለየ መልኩ የኢትዮጵያ የኦፓል ክምችት ተቆፍሮ መውጣት የጀመረው በቅርብ ዓመታት ጊዜ ውስጥ ነው፡፡እንደ አንትሮፖሎጂስቶች ዘገባ ከሆነ ግን ከክርስቶስ  ልደት በፊት 4 000 ዓመታት ግድም በአካባቢው ይኖር የነበረው ጥንታዊው የሰው ልጅ ከኦፓል የመገልገያ መሳሪያዎች ይሰራ እንደነበር ይታወቃል፡፡

    ምንጭ፡- www.DireTube.com

No comments:

Post a Comment