Thursday, December 26, 2013

ሳክስፎኒስት ቴዎድሮስ ምትኩ - በጌጡ ተመስገን

‹‹ቦብ ማርሌይ ጊዮን ሆቴል ሲዋኝም፤ ሙዚቃ አድምጦ ሲወጣ ልብ ያለው ሰው አልነበረም›› የቦብ ማርሌይ “No woman, No cry” ‹‹ ውማን ክርይ›› የተሰኘውን ዘፈን ሙሉቀን መለሠ ከሪዳ ኢብራሂም ጋር በጊዮን ሆቴል ክለብ ይጫወቱት ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ ቦብ ማርሌይ ኢትዮጵያ መጥቷል፡፡ ቦብ ማርሌይ እነሙሉቀን ሲጫወቱ ተመልካች ሆኗል፡፡ (እነርሱም) ቦብ ማርሌይ በክለብ ውስጥ ተገኝቶ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ያጣጥማል፤ ይመሰጣል ብለው አልጠበቁም፡፡
  አንድ እንግዳ ሰው - ለመዝፈን ባንዱን ፈቃድ ጠየቀ፡፡ ተፈቀደለት፡፡ ጃማይካዊው እንግዳ ሲዘፍን ድምፁን የሚያውቁት ዓለም አቀፍ አርቲስት ቦብ ማርሌይ እንደሆነ አወቁ፡፡ በዚያን ወቅት በጊዮን ሆቴል ክለብ ውስጥ ሲጫወቱ የነበሩት ሙሉቀን መለሠ፣ ሪዳ ኢብራሂም፣ አበራ ፈይሣ፣ ዳዊት ካሣ፣ ጥላዬ ገብሬ፣ ሽመልስ በየነና ተስፋዬ ተሠማ ነበሩ… (ይሁን እንጂ ቦብ ማርሌይ ጊዮን ሲዋኝም፤ ሙዚቃ አድምጦ ሲወጣ ልብ ያለው ሰው አልነበረም) ቦብ ማርሌይ የሙሉቀን መለሠ ችሎታን አደነቀ፡፡

   ‹‹ሻሸመኔ›› የተሰኘ አልበም ለመሥራት ተስማሙ፡፡ ቦብ ማርሌይ ለሙሉቀን ግጥሞች ሠጥቶት ወደ ጃማይካ ሄደ፡፡ ከዚያም ሙሉቀን የዘፈኖቹን ግጥም ማጥናት ጀመረ፡፡ ይሁን እንጂ የቦብ ማርሌይ ዜና እረፍቱ ተሰማ፡፡ ሳክስፎኒስት ቴዎድሮስ ምትኩ - ያጫወተኝን ታሪክ ነበር
   
    ቴዎድሮስ የሙዚቀኛው Teshome Mitiku ታላቅ ወንድም ነው፡፡ (የቀበና ልጆች) … (ETHIOPIAN LEGEND: Teshome Mitiku Singer and songwriter ‘’Gara Sir New Betesh – Mot Adeladlogn – Yezemed Yebada - Yemekabir Echognaye – SUSEGNASH - Hasabe - etc’’ … his famous daughter, the Swedish Emilia and his brother, saxophonist Tewodros Mitiku (በነገራችን ላይ ተሾመ ምትኩ ከኢትዮጵያ ከወጣ 40 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል) … ሳክስፎኒስት ቴዎድሮስ ምትኩ (30ዓመት በፊት) .. 1983 ወደ አሜሪካ ቴክሳስ ግዛት አመራ፡፡
    
   
   እ.. 2007 ኢትዮ - አሊያንስ ፍራንሴዝ ታዋቂው ግርማ በየነን እና ሦስት ዝነኛ ሳክስፎኒስቶች ጥላዬ ገብሬ፣ ቴዎድሮስ ምትኩና ሞገስ ሀብቴን አምጥተዋቸው ነበር፡፡ የእነርሱ የማይጠገበው የሙዚቃ ሥራ እንዲሁም (የህዝቡ ፍቅርና አድናቆት ምላሽ) በቦታው የነበረ ሰው የሚረሳው አይደለም፡፡ ሁለት በመሣሪያ የተቀነባበሩ ምርጥ ሥራዎችን በካሴትአበርክቶልናል፡፡ የሳክስፎኒስት ቴዎድሮስ ምትኩ ባለቤት (የጥላሁን ገሠሠ ባለቤት ሮማን በዙ) እህት ስትሆን፤ ከማዕዛ በዙ ጋር 22 ዓመታት በትዳር ዓለም ቆይተዋል። ቴዎድሮስ ምትኩ ባደረበት ህመም በሜሪላንድ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ አርፏል፡፡ (ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበርየሳክስፎኒስት ቴዎድሮስ ምትኩ - አማሌሌ - የሙዚቃ ሥራውንአድምጡ፡፡                      
                                   http://youtu.be/xbRnPCmnutw 
                                                     
   

No comments:

Post a Comment