ለአፍሪካ ዘላቂ
ልማትና ዕድገት የሳይንስና ቴክኖሎጂ
ዘርፍ ከፍተኛ ሚና እንዳለው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ወ/ሮ ደሚቱ ሃምቢሳ ገለጹ፡፡
በአዲስ አበባ ዘንድሮ ለ7ኛ ጊዜ እየተካሄደ ያለው የአፍሪካ ማቴሪያል ሪሰርች ሶሳይቲ ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ምሁራን፣ ተማሪዎች እና በሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆኑ ለአፍሪካ ችግሮች መፍትሔ በሚሆኑ ጉዳዮች ላይም ይመክራሉ፡፡
በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሯ ወ/ሮ ደሚቱ ሃምቢሳ ለአፍሪካ ዘላቂ ልማት እና ዕድገት የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከፍተኛ ሚና እየጠጫወተ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ የሣይንስ እናቴክኖሎጂ ዘርፍ መጫወት የሚገባውን ሚና ለማሳደግ ኢትዮጵያም ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት በመስጠት በርካታ ስራዎች እያከናወነች መሆኗን ገልጸዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ምክትል ሊቀመንበር ኢራስተስ ሙዌንቼ ሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ለሃገራት ዕድገትና የማሕበራዊ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡ በመሆኑም ሀገራት ይህንን ዘርፍ በሚፈለገው ደረጃ በማሳደግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በጋራ የመስራት አቅማቸውን ማጎልበት እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡
ለዓለም ማሕበረሰብ በሣይንስ እና ቴክኖሎጂው ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ለተባሉ ሶስት ሴት ፕሮፌሰሮች የአፍሪካ ህብረት ኩዋሜ ኑክሩማ መታሰቢያ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ሽልማቱ ለእያንዳንዳቸው 20 ሺህ ዶላር የገንዘብ ስጦታን ያካተተ ሲሆን ተሸላሚ የሆኑት ፕሮፌሰር ኢዛቤል አዲሌ ግሊቶ ከሎሜ ቶጎ ዩኒቨርሲቲ፣ ፕሮፌሰር ቦንዜ ኢ ሪባሊ ከቡርኪና ፋሶ ኡጋዱጉ ዩኒቨርስቲ እና ፕሮፌሰር ኮራሽ አብዱል ከሪም ከደቡብ አፍሪካ ናቸው፡፡
No comments:
Post a Comment