Monday, December 2, 2013

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ስደተኞች ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ሆና ተመረጠች


 አቀፍ ስደተኞች ድርጅት ጉባዔ በጀኔቫ ስዊዘርላንድ በተካሄደበት ወቅት ኢትዮጵያን የ2013/14 የዓለም አቀፉ ስደተኞች ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር በማድረግ መርጧል፡፡
  በዚህም ተቀማጭነታቸው በጄኔቭ የሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቋሚ መልዕክተኛ በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ምኒሊክ ዓለሙ የምክር ቤቱ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡
    አምባሳደር ምንሊክ ኢትዮጰያውያንን ጨምሮ ከብዙ ታዳጊ ሃገራት እየተሰደዱ ያሉ ዜጎች በህገ ወጥ ደላሎችና አቀባባዮች እንዲሁም በተቀባይ ሃገራት እየደረሰባቸው ያለውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰትና በደል ኮንነዋል።  የኢትዮጵያ መንግስት ህገ-ወጥ ስደትን ለመከላከል ከፍተኛ ሥራ እየሰራ መሆኑንም ለምክር ቤቱ አብራርተዋል፡፡
    በተመሳሳይ ዜና በጄኔቭ የሚገኙ የኢጋድ አምባሳደሮችና ቋሚ መልዕክተኞች፣ የተባበሩት መንግሰታት ድርጅት ጽሕፈት ቤት አባል ሀገሮች እና በስዊዘርላንድ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተገኙበት የኢጋድ ፎረም ተካሂዷል፡፡ በፎረሙ ላይ የጅቡቲ፣ የሶማሊያ፣ የኬንያ፣ የኡጋንዳ፣ የደቡብ ሱዳን፣ የቡሩንዲ፣ የሱዳን እና የታንዛኒያ አምባሳደሮች መሳተፋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

No comments:

Post a Comment