የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የቀድሞው የአገሪቱ ምክትል
ፕሬዚዳንት ታማኞች የነበሩ ወታደሮች ያካሄዱት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሸፉን ይፋ አደረጉ።
ሌሊቱን የአገሪቱ መዲና ጁባ በተኩስ ውስጥ ማደሯን ተከትሎ ነው ኪር መግለጫውን የሰጡት። በመዲናዋ ጁባ ሲካሄድ የነበረው የተኩስ ልውውጥ እስከዛሬ ማለዳ ድረስ ዘለቆ ነበር። ፕሬዚዳንት ኪር እንዳሉት ዩኒፎርም ያላደረጉ ወታደሮች በሱዳን ህዝብ ነፃ አውጪ ንቅናቄ /ኤስ ፒ ኤል ኤም/ ስብሰባ ላይ ተኩስ ከከፈቱ በኋላ ግጭት መቀስቀሱን ነው ያስረዱት። መንግሰት በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ የአገሪቱን መዲና መቆጣጠሩን አረጋግጠዋል።
ፕሬዚዳንቱ ኤስ ፒ ኤል ኤም በደቡብ ሱዳን ስልጣን በሀይል እንዲተላለፍ አይፈቅድም ብለዋል በመግለጫው ላይ። ሳልቫ ኪር ታማኝ አፍርተዋል ያሏቸውን ምክትላቸው የነበሩት ሪክ ማቻር ፕሬዚዳንቱ በቅርቡ ካቢኒያቸውን ሲያፈርሱ አብረው ከስልጣን መነሳታቸው ይታወሳል።
ወታደራዊ ዩኒፎርም ለብሰው መግለጫ የሰጡት ኪር ከዛሬ ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መውጣቱንም ይፋ አድርገዋል። ከጁባ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት በመዲናዋ የሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ የተዘጋ ሲሆን፥ የአገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያም ለሰዓታት ተቋርጦ ነበር።
ምንጭ ፡- ኤፍ.ቢ.ሲ

No comments:
Post a Comment