Friday, January 31, 2014

ሶስት ኢትጵያዊ የፋስት ካምፓኒ መፅሄት ምርጥ 1,000 ስራ ፈጣሪዎች ውስጥ ተካተቱ፡፡

    ቤቴልሄም ጥላሁን ፣ማርቆስ ሳሙኤልሰን እና ብሩክታዊት ጥጋቡ የፋስት ካምፓኒ መፅሄት ምርጥ 1,000 ስራ ፈጣሪዎች ውስጥ አካተተ።

        ቤቴልሄም ጥላሁን አለሙ የሶልርበልስ የጫማ አምራች ድርጅት ባለቤት ስትሆን 20 በአፍሪካ ተፅ
ኖ ፈጣሪዎች ውስጥ መካተቷ ይታወሳል፡፡ ማርቆስ ሳሙኤልሰን በአለማችን ታዋቂ ከሆኑ ሼፎች ውስጥ አንዱ ሲሆን  ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት እና ቤተሰቦቹ ምግብ እንዲያዘጋጅ የተመረጠ ብቸኛ ጥቁር ሼፍ ነበር ፡

  ብሩክታዊት ጥጋቡ ደግሞ የፀሀይ መማር ትወዳለች መስራች ናት፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ከፌስቡክ እና ከማይክሮ ሶፍት ፈጣሪዎች ጋር አብረው የተካተቱ ናቸው ፡፡    



 http://www.fastcompany.com/3025456/most-creative-people/most-creative-people-in-business-1000-the-complete-list






















የዓለም አቀፉ የኑክሌር ፍንዳታ እገዳ ድርጅት በኢትዮጵያ ምርምሮችን ለማከናወን ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

       
   የዓለም አቀፉ የኑክሌር ፍንዳታ እገዳ ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ የመረጃ ማዕከል በማቋቋም ምርምሮችን ለማከናወን ፍላጎት እንዳለው ገለፀ፡፡ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ላሲና ዜርቦን  ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሯ  ደሚቱ ሃምቢሶ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይተዋል።

    ማዕከሉ የኒውክሌር ፍንዳታን፣  እሳተገሞራ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመተንበይ የሚያስችል ተግባራትን ያከናውናል፡፡ 

      
     ድርጅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚሰበስበው የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች መረጃ ለሚሰጠው አገልግሎት ጥራት እንደሚጠቅመው ተገልጿል። ኢትዮጵያ ደግሞ መረጃን ጨምሮ የድርጅቱን የቴክኒክና የስልጠና ድጋፍ እንድታገኝ ያሰችላታል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነፃ - የሰበዓዊ ግልጋሎት አካሄደ፡፡


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያስመጣው
777-300 ER የተሰኘው ቦይንግ አውሮፕላን ወደ ኢትዮጵያ በሚያደርገው ጉዞው የተለያዩ የዕርዳታ ቁሳቁሶችን ይዞ እንደመጣ ታውቋል፡፡

 አውሮፕላኑ በጉዞው ይዟቸው ከመጣው ቁሳቁሶች ውስጥ ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የተላኩ የህክምና ቁሳቁሶችና ለጎባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግልጋሎት እንዲውሉ የተላኩ ከመቶ በላይ ኮምፕዩተሮች ይገኙበታል፡፡

         የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህን መሰል የነጻ የሰብዓዊ ግልጋሎት የአየር በረራ ከቦይንግ ጋር በመሆን ሲያካሂድ 19ኛው ጊዜ እንደሆነ ታውቋል፡፡
                                                                                                                
                                                                                         

ሴፕ ብላተር በደቡብ አፍሪካ የማንዴላን ቤተሰቦች ጎበኙ


 የቻን የፍጻሜ ጨዋታን ለመታደም ደቡብ አፍሪካ የተገኙት የዓለምአቀፉ እግር ኳስ ፌደሬሽን /ፊፋ/ ፕሬዝዳንት  ሴፕ ብላተር የማንዴላን ቤተሰቦች ዛሬ ጎበኙ፡፡  
     በጉብኝቱ የፊፋው ዋና ፀሀፊ ጀርሞ ቫልክ፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን /ካፍ/ ፕሬዘዳንት ኢሳ ሀያቶ፣ የደቡብ አፍሪካው እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዘዳንት ዳኒ ጆርዳን እንዲሁም የተለያዩ የዘርፉ አካላት ተካፋይ ሆነዋል፡፡እዚህ የተገኘነው ዓለም ያጣችውን ታላቅ መሪ ቤተሰቦች ለማግኘትና ደጋፋችንን ለመግለጽ ነው ብለዋል ሴፕ ብላተር ፡፡ ጨምረውም ማንዴላ ለሰባዊ መብት የከፈለው መሰዋትነት በእኛ ታላቅ ክብር አለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የማንዴላ ልጅ የሆነው ዚንዲ ፊፋ ለቤተሰቦቹ  እያደረገ ያለውን ደጋፍ በማመስገን፣ እግር ኳስ ህዝቦችን የማቀራረብ ሃይል ስላለው ለዓለም አቀፍ ሰበዊ እርዳታ እንቅስቃሴ  ልንጠቀምብት ይገባል ብሏል፡፡ ማንዴላ ለሰባዊ ተግባራት የከፈሉትን መሰዋትነት በማስታወስ፡፡
                                                    
                                                         ምንጭ ፡- ኢሬቴድ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዓለማችን 107ኛ ጠንካራ ሊግ ተባለ



    የዓለም አቀፉን እግር ኳስ ፌደሬሽንን ታሪክና ስታስቲክስ የሚመዘግበው ድርጅት አይ ኤፍ ኤፍ ኤች ኤስ /IFFHS/ .. 2013 ውጤት ተከትሎ ባወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዓለማችን 107ኛው ጠንካራ ሊግ መሆኑን አሳውቋል፡፡

ድርጅቱ ደረጃውን የሚያወጣው የየሀገራቱ ክለቦች በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ውድድሮች በሚያስመዘግቡት ውጤት መሰረት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ባለፈው ዓመት ከተሰጠው የ110ኛ ደረጃ በዚህ ዓመት 3 ደረጃዎችን ማሻሻል ችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ደረጃ ከወጣላቸው ሀገራት 18ቱን በመብለጥ ነው የ107ኛ ደረጃ የተሰጠው፡፡ በድርጅቱ ሪፖርት መሰፈርት የስፔን ላሊጋ ቀዳሚውን ሲይዝ፣ የእንግሊዝ ፕሪምር ሊግ ደግሞ ተከታይ ደረጃን ይዟል፡፡ የጀርመን ፣ ጣሊያንና ብራዚል ሊግም በቀደም ተከተል ከ3-5ኛ ደረጃ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ከአፍሪካ ሀገሮች በሊጋቸው  ቀዳሚ ስፍራ የተሰጣቸው ቱኒዚያ፣ ግብጽና ናይጀሪያ ናቸው፡፡ሩዋንዳ፣ ቶጎ፣ ሴኔጋልና ኡጋንዳ በቀደም ተከትል ደካማ ሊግ ያላቸው ሀገሮች በመባል ተቀምጠዋል፡፡

Thursday, January 30, 2014

ሞሪታንያ የህብረቱን የሊቀመንበርነት ቦታ ተረከበች

   ግብርናና የምግብ ዋስትና በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ፤ የአህጉሪቱ መሪዎች በቀጣይ የግብርናውን ዘርፍ ስር ነቀል በሆነ መልኩ በመቀየር የአፍሪካን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በቀጣይ መግባባት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ከሰላምና ጸጥታ ጋር ተያይዞም መረጋጋት የራቃቸውን ሃገራት ወደ ሰላም መመለስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መሪዎቹ ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚያሰቀምጡም ነው የሚሆነው ።

     የአየር ንበረት ለውጥ ፤ የመሰረተ ልማት ትሰስር እና ንግድም ጉባኤተኞቹ ከሚነጋገሩባቸው ነጥቦች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው ። በጉባኤው ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶክተር ኒኮሳዛ ዲላሚኒ ዙማ የአፍሪካ ሀገራት በግብርና ላይ የሚያደርጉትን ኢንቨስትመንት በማሳደግ የ7 በመቶ ዓመታዊ ዘላቂ ምጣኔ ኃብታዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚኖርባቸው ነው ያሳሰቡት።

      በግብርናው መስክ ባለው ስራ ላይ በስፋት የተሰማሩ የአፍሪካ ሴቶች በቂ የክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ እና ሀብት እንዲያፈሩ የሚደረገውን ጥረት ህብረቱ እንደሚደግፍም አረጋግጠዋል። አፍሪካ ለእድገቷ እንቅፋት በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ከተቀረው የዓለማችን ክፍል ጋር ያላትን የንግድና የትብብር ስራዎችን በላቀ ደረጃ ማስኬድም ይጠበቅባታል ብለዋል ሊቀመንበሯ።

   ከሰላምና መረጋጋት ጋር በተያያዘም በተወሰኑ የአህጉሪቱ ክፍሎች የሚስተዋሉ ግጭቶችና አለመግባባቶች ትልቅ ዋጋ እንደሚያስከፍሉ የታወቀ ነው ያሉት ዶክተር ኒኮሳዛ ፥ ስለሆነም ለሰላምና መረጋጋት የሚሰጠውን ዋጋ በዚያው ልክ በመጨመር ዲሞክራሲያዊ  እና ሀላፊነትን የሚሸከም አስተዳደርን ለመገንባት መረባረብ  እንደሚገባም ነው የጠቆሙት ።

      አፍሪካ የ2063 አጀንዳን ማሳካት እንድትችል ህብረቱ ሁሉም አፍሪካዊ እና ትውልደ አፍሪካዊ ሁሉ የሚጠበቅብትን ሁሉ በማድረግ ለዕቅዱ መሳካት ርብርብ እንዲያደርግም  ዶክተር ኒኮሳዛ ድላሚኒ ዙማ ጥሪ አቅርበዋል። የህብረቱ የወቅቱ ሊቀመንበር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በበኩላቸው ፥ በአሁኑ ወቅት ጥቂት የማይባሉ የአፍሪካ አገራት ከአጠቃላይ ባጀታቸው 10 በመቶ ያህሉን በግብርናው ዘርፍ ላይ መመደባቸው "ግብርናና የምግብ ዋስትና” በሚል መርህ በአፍሪካ ለሚደረገው የለውጥ እና የዕድገት ጉዞ አጋዥ መሆኑን ጠቁመዋል።

     ሰላምና መረጋጋትን በአህጉሪቱ ለማረጋገጥም ህብረቱ  የሚጠበቅበትን ሁሉ እየተወጣ ይገኛል  ፤ በተለይም ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በደቡብ ሱዳን የተከሰተውን አለመረጋጋት በሰላም እንዲፈታ ለማድረግ የተደረገው ጥረት ውጤት እያስገኘ መሆኑን መመልከት ይቻላል ብለዋል አቶ ሀይለማርያም።

      በአለፈው አንድ አመት ውስጥ አፍሪካውያን መልካም የሚባል ውህደት ፈጥረዋል  ፤ የተለያዩ የጋራ አጀንዳዎችም በስኬት ተከናውነዋል ያሉት አቶ ሀይለማርያም ፥ በመካከለኛዋ አፍሪካ ሪፐብሊክ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲረጋገጥ እና አገሪቱ ቀድሞ ወደነበረችበት መረጋጋት እንድትመለስ አለማቀፉ ማህበረሰብ ጥረቱን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት።

      በተጨማሪም አህጉሪቱ  የ2063 አጀንዳን እንድታሳካ ፣ የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ለውጥን ውጤታማ በሆነ መንገድ ማረጋገጥ እንድትችልና የበለፀገች አፍሪካን ማየት እንዲቻል ከአፍሪካውያን የበለጠ ስራ እና ጥረት ይጠበቃል ብለዋል። በጉባኤው አፍሪካ በመልካም አስተዳደር እምርታ አሳይታለች ፤ ስለሆነም አህጉሪቱን መላው የዓለም ህዝብ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አይናቸውን እንደጣሉባት የተናገሩት ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ምክትል ጽሀፊ  ጃን ኢሊሰን ናቸው።

    በሌላ በኩል የማዳጋስካርን ወደ ህብረቱ መመለስ ምክንያት በማድረግ ፕሬዝዳንት ሄሪ ራጃኦናሪማምፒያኒና  ባደረጉት ንግግር ሀገራቸው ጠንካራ መንግስት ለመመስረት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኗን ተናግረዋል። የሊቀመንበርነቱን ቦታም የሞሪታንያው ፕሬዝዳንት ሙሀመድ አብድልአዚዝ ከህብረቱ  የወቅቱ ሊቀመንበር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ተረክበዋል። ጉባኤው በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በነገው እለትም   የሚቀጥል ይሆናል።

                                                                                                                            ምንጭ ፡- ኤፍ.ቢ.ሲ    


          ስድስት የትምህርት ሚንስቴር ሰራተኞች ህይወታቸው አለፈ፡፡

      በትላንትናው ዕለት አባይ ወንዝ አቅራቢያ በደረሰ የመኪና አደጋ 6 የትምህርት ሚንስቴር ሰራተኞች ህይወታቸው አልፏል፡፡

    ለሴሚናር ከአዲስ አበባ ወደ ደብረማርቆስ የሚጓዙ የትምህርት ሚንስቴር ሰራተኞችን የያዘው መኪና ትላንት ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ በፍሬን ችግር 25 ሜትር ገደል ውስጥ በመግባቱ ነበር አደጋው የተከሰተው፡፡  በአደጋው ከሟቾቹ በተጨማሪ 1 ከባድና 18 ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሷል፡፡
                                                         
                                                                     ዝርዝሩን ➤➤➤ http://diretu.be/788622

Wednesday, January 29, 2014

አትሌት እጅጋየሁ ድባባ የበኩር ልጇን ለማቀፍ በቃች፡፡

 

     ከማን ካላችሁ ከዝነኛው ድምፃዊ ቀመር የሱፍ ነው፡፡
   

    5 ዓመታት በትውውቅ እንዲሁም በፍቅር የቆዩት ዝነኛው ድምፃዊ ቀመርሱፍ እና አትሌት እጅጋየሁ ዲባባ ሶሊያና የተባለችውን የመጀመሪያ ሴት ልጃቸውን አቅፈው ለመሳም በቅተዋል፡፡

   
ካናዳ ውስጥ የሚኖረው ቀመር በቅርቡ አዲስ አልበም እንደሚያወጣ ለአድናቂዎቹ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
 
                             ከቀመር ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ ➤➤➤ http://diretu.be/998874

በአዲስ አበባ የፈጣን አውቶቢስ አገልግሎት ሊጀምር ነው



    ለአዲስ አበባ ከተማ የትራንሰፖርት ችግር ዘለቄታዊ መፍትሄ ለማምጣት የሚያስችል የፈጣን አውቶብስ ትራንስፖርት ፕሮጀክት በተግባር ላይ ሊውል ነው። ትናንት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት በከንቲባው ጽህፈት ቤት አዳራሽ ባዘጋጁት የግማሽ ቀን ውይይት ላይ ነው ፕሮጀክቱ  ይፋ የተደረገው።

    ፕሮጀክቱ የከተማይቱን የትራንስፖርት ስርዓት የሚቀይር ቀጣይነት ያለው ዘመናዊና የተቀናጀ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር እንደሚያስችል የተገለጸ ሲሆን በስራ ላይ ሲውልም ከተማይቱ የፈጣን አውቶብስ አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሚያደርጋት ተገልጿል።
አውቶብሶቹ በቴክኖሎጂ የረቀቁና በኮምፒውተር የሚታገዙ ሲሆን የራሳቸው የሆነ መስመርና ኮሪደር እንደሚኖራቸውም ነው የተጠቆመው።

    በፕሮጀክቱ ዲዛይን መሰረት በአዲስ አበባ ዘጠኝ ኮሪደሮች ሲኖሩት ከዘጠኙ ኮሪደሮች  መካከል የመጀመሪያው የሙከራ ትግበራ የሚሆነውና 12 . የሚሸፍነው ከጎፋ ገብርኤል ተነስቶ በሜክሲኮና መርካቶ አድርጎ መጨረሻውን ዊንጌት የሚያደርገው ኮሪደር ነው ይህም የፓይለት ፕሮጀክት ኮሪደር እስከ ሰኔ 2006 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

    ፈጣን አውቶብሶቹ ስራ ሲጀምሩም በመስመራቸው በየሁለት እና ሶስት ደቂቃ ልዩነት አንድ ፌርማታ እንደሚደርሱና  ተሳፋሪዎች  አውቶብስ ለመጠበቅ ቢበዛ 4-5 ደቂቃ ብቻ እንደሚወስድባቸው ተብራርቷል ፈጣን አውቶብሶቹ  በከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ላይ በመሰማራት የትራንስፖርት አገልግሎቱን ያግዛሉም ነው የተባለው።

   ይህ የፈጣን አውቶብስ አገልግሎት ፕሮጀክት እስከ 2008 . ድረስ እንደሚጠናቀቅና በአሁኑ ወቅት 50 በመቶ እንደተጠናቀቀ የሚነገርለትን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ግንባታ በማገዝ የከተማዋን የትራንሰፖርት አገልግሎት ዘመናዊ ምቹ እና ቀልጣፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
                                          ምንጭ ፡- ኤፍ.ቢ.ሲ