Sunday, May 12, 2013

የአቶ ገብረዋህድ ባለቤት በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ ባለቤት ኮሎኔል ሃይማኖት ተስፋይ ባለቤታቸው ከተጠረጠሩት ወንጀል ጋር ተያያዥ የሆኑ ሰነዶችን ሲያሸሹ በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ከፖሊስ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ኮሎኔል ሃይማኖት ከመኖሪያ ቤታቸው ወስደው በሌሎች ግለሰቦች እጅ እንዲደበቁ ያሸሻቸው ሰነዶች በተለያዩ ቦታዎች በአቶ ገብረዋህድ ስም የተመዘገቡ የቤትና የቦታ ካርታዎች ናቸው፡፡
ኮሎኔል ሃይማኖት ካርታዎችን ሲያሸሹ ጥቆማ የደረሳቸው የደህንነትና የፖሊስ ሃይሎችም ክትትል በማድረግ ካርታዎቹን ከተደበቁበት ቦታ ይዘዋቸዋል፡፡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ግንቦት 2/ 2005 በቁጥጥር ስር በዋሉት ግለሰቦች ቤት በተደረገው ብርበራ ከፍተኛ መጠን ያለው የኢትዮጵያና የውጭ ሃገራት ገንዘብ እንዲሁም የተለያዩ ሰነዶች መገኘታቸው ይታወሳል፡፡

No comments:

Post a Comment