Tuesday, May 13, 2014

ኢትዮጵያ ፈጣን ኢኮኖሚ በማስመዝገብ በአህጉሪቱ ቀዳሚ ሆነች

የ2014ቱ የአፍሪካ የኢኮኖሚ ሪፖርት ኢትዮጵያን የአፍሪካ ፈጣኑ የኢኮኖሚ እድገት በሚል ገልጧል፡፡

  የ2014 የአፍሪካ የኢኮኖሚ ሪፖርት መሰረት "ለውጥ በኢንዱስትሪ ያለሰዎች ፈጠራን የሚያጎለብቱ ተቋማትና ተለዋዋጭ ዘርፎችን በመተግበር" በሚል ርእስ ነው የመጣው፡፡ ሪፖርቱ በአፍሪካ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ የሚድረግ መሰረታዊ ሽግግር ለአህጉሪቱ ብልፅግና ወሳኝ ነው የሚል አቋም ይዟል፡፡

  ሪፖርቱ በ4 ዓመታት በአፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘገቡትንና በጣም ዝቅተኛ ውጤት ያመጡትንም ዳሷል፡፡በዚህም ኢትዮጵያ እንደ ጎርጎሮሳዊኑ የዘመን ቀመር ከ2009­ እስከ 2013 ድረስ 9.4 በመቶ አማካኝ ዕድገት በማስመዝገብ ከሁሉም የአህጉሪቱ ሀገራት ቀዳሚ ሆና ተቀምጣለች፡፡
 
 በእርስ በርስ ጦርነት የምትታመሰው መካከለኛዋ አፍሪካ ደግሞ የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች፡፡በሪፖርቱ የአፍሪካ የእርስ በርስ የንግድ ልውውጥም ተዳሷል ፡፡ እስከ 2012 ባለ መረጃ እንኳን ወደ 11.5 በመቶ ወይንም 73.3 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተጠቁሟል፡፡ ከዚህ ውስጥ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ውጤቶች የ40 በመቶ ድርሻ ይዘዋል፡፡እናም ለኢንዱስትሪ ልማት የሚሰጠው ትኩረት ለንግድ ትስስሩም መሰጠት ቁልፍ መሆኑን በኢስኤ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ዳይሬክተር አዳም አልሃራይ ገልፀዋል፡፡ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ትኩረት በመሥጠት ለመዋቅራዊ ሽግግሩ እየሰራች ነው እንደሆነ  የኢንዱስትሪ ሚንስትር ድኤታ ልዩ አማካሪ አህመድ ኑሩ አስረድተዋል፡፡ 

No comments:

Post a Comment