Sunday, April 14, 2013

አትሌት ሃይሌ የቪየናን ግማሽ ማራቶን አሸነፈ



አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ የቪየናን ግማሽ ማራቶን ለሶስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈ።

   አትሌት ሃይሌ ከውድድሩ አጋማሽ ጀምሮ በመምራት በ1 ሰአት ከ1 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ሲያሸንፍ ኬንያዊው ሆሲያ ኪፕኬምቦይ በ1 ሰአት ከ2 ደቂቀ ከ21 ሰከንድ 2ኛ እንዲሁም ኢትዮጵያዊው መኳንንት አየነው በተመሳሳይ ሰአት 3ኛ ሆነው አጠናቀዋል።

    ሃይሌ ውድድሩን ካሸነፈ በኋላ በሰጠው አስተያየት በስፍራው ከተመልካቾች ያገኘው ማበረታቻ እና ውድድሩ አስደሳች እንደነበር ገልጿል። ባለፈው የመጋቢት ወር ላይ ከስፖርቱ ጋር በፍቅር እንደወደቀ የተናገረው ሃይሌ በውድድር እስከተደሰትኩ ድረስ መሮጤን እቀጥላለሁ የሩጫ ቆይታዬ እንዴት እና መቸ እንደሚያበቃ ግን አላውቅም’’ ብሏል።

  አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ በ1998ቱ የፎኒክስ ግማሽ ማራቶን ያስመዘገበው 58 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ የምንጊዜም ምርጥ ሰአቱ ነው።

No comments:

Post a Comment