Friday, April 19, 2013


የመጀመሪያው የአደጋ ስጋት አመራር ማዕከል በአዲስ አበባ ተከፈተ

 
  በአፍሪካ የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ስጋት ለመከላከል እገዛ የሚያደርግ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነ የአደጋ ስጋት አመራር ማዕከል በአዲስ አበባ ተከፈተ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት የአፍሪካ የአደጋ ስጋት አመራር ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ካሳሁን በዳዳ እና የአየር ንብረት ሳይንስ ማዕከል ዳይሬክተር ዶክተር ዘውዱ እሸቱ በሰጡት መግለጫ ማዕከሉ በአዲስ አበባ መከፈቱ ኢትዮጵያ በአደጋና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እያደረገች ያለውን ተግባር ያጠናክራል ብለዋል፡፡
 
      ማዕከሉም በዋናነት በአደጋ ስጋት አመራር ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች የአቅም ክፍተትን ለመሙላትና በአየር ንብረት ለውጥና በአደጋ ስጋት መከላከል ላይ በትብብር ለሚሰሩ አካላት እንዲሁም የመረጃ ማዕከል በመሆን ያገለግላል ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም በማዕከሉ የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በማከናወን ለአደጋ ስጋት ለሆኑ አካባቢዎች የራሱን ሚና እንደሚወጣም ጠቁመዋል፡፡ የአደጋ ስጋት አመራር ማዕከል ራሱ በሚያከናውናቸው የምርምርና የስልጠና ተግባራት ገቢ ያመነጫል፡፡

No comments:

Post a Comment