አየርላንድ ደብሊን ከተማ ውስጥ በተካሄደው አመታዊው የታላቁ ሩጫ የ10
ኪሎ ሜትር ውድድር በተደጋጋሚ ጉዳት የአለፉት ጥቂት አመታትን ያሳለፈው የረጅም ርቀት ሩጫው ሀያል ቀነኒሳ በቀለ
ርቀቱን 28 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ ከአስደናቂ ብቃት ጋር አንደኛ ወጥቶ አሸንፏል።
ከ10 አመት በፊት በአለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና አየርላንድ ውስጥ የሁለት ወርቅ ሜዳሊያዎች ባለቤት የሆነው እና አምና በተመሳሳይ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር የመጪዎችን ክብረወሰን በመስበር አንደኛ በመውጣት ያሸነፈው ቀነኒሳ በቀለ አየርላንድ ውስጥ ባደረጋቸው አጠቃላይ ውድድሮች አንድም ጊዜ አልተሸነፈም። በድሉ የተደሰተው ቀነኒሳ በቀለ አጠቃላይ በውድድሩ ላይ ያሳየው ብቃትም እንዳረካው ከውድድሩ በኋላ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል። ከሁለት አመት በፊት ዴጉ ውስጥ በተካሄደው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለኢትዮጵያ በ10 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘው እና ከዛ ድሉ በኋላ በአብዛኛው በጉዳት ምክንያት ከውድድሮች ርቆ የቆየው ኢብራሂም ጄላን (29:18) ቀነኒሳ በቀለን እና ዩክሬናዊው ሰርጌ ሌቤድን በመከተል ሶስተኛ ደረጃን አግኝቶ አጠናቋል።
ወደ ኦስትሪያ ያቀናው ታላቁ የረጅም ርቀት ሯጭ ሀይሌ ገብረስላሴ ለሶስተኛ ተከታታይ አመታት የቪዬና ግማሽ ማራቶን ሻምፒዮን ሆኗል። በቅርቡ 40ኛ አመት የልደት በአሉን የሚያከብረው የሁለት ኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎች ባለቤት ሀይሌ ግማሽ ማራቶኑን በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ 61 ደቂቃ ከ 14 ሰከንድ ወስዶበታል።ሀይሌን ተከትለው ኬኒያዊው ሆሲያ ኪምኬምቦይ ሁለተኛ፣ ሌላው ኢትዮጵያዊ መኩዋንንት አየነው ሶስተኛ ደረጃን አግኝተው አጠናቀዋል።
ሀይሌ ከድሉ በኋላ በሰጠው አስተያየት “ምንም እንኳን ከዚህ በፈጠነ ለመሮጥ ብፈልግም ዛሬ ሊሳካልኝ አልቻለም። ምናልባት ቀዝቀዝ ብዬ ብጀምር ኖሮ በኋላ ላይ ፍጥነቴን መጨመር እችል ነበር። በአጠቃላይ ግን የውድድሩን ሁኔታ እና አሯሯጤ አስደስቶኛል” ብሏል። ለምን ያህል ጊዜ በሩጫው እንደሚቀጥል የተጠየቀው ሀይሌ ገብረስላሴ “ደስተኛ እስከሆንኩ ድረስ መሮጤን እቀጥላለሁ። መቼ እና እንዴት እንደማቆም ግን አላውቀውም” በማለት መልሷል። እዛው ቪዬና ውስጥ በተካሄደው የማራቶን ውድድር በሴቶች ኢትዮጵያዊያኖቹ መስከረም አሰፋ (2:31:18) እና እየሩሳሌም ኩማ (2:32:24) ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በማግኘት አጠናቀዋል።ይሄንን ውድድር ኬኒያዊቷ ፍሎሜና ቼዬች በፍጹም የበላይነት ርቀቱን በ2 ሰአት ከ24 ደቂቃ ከ34 ሰከንድ ጨርሳ አንደኛ በመውጣት አሸንፋለች።
ሆላንድ ሮተርዳም ውስጥ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው ጥላሁን ረጋሳ ርቀቱን 2፡05፡38 በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆኗል። ይህ የማራቶን ውድድር ለጥላሁን በታሪኩ ሁለተኛው ነው። ጥላሁንን ተከትሎ የሀገሩ ልጅ ጌቱ ፈለቀ ልክ እንደ አምናው ሁሉ ሁለተኛ ደረጃን አግኝቶ አጠናቋል። ጌቱ ርቀቱን ሮጦ ለመጨረስ 2፡06፡45 ወስዶበታል።
በሴቶቹ የሮተርዳም ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አበበች አፈወርቅ በ2፡23፡59 ርቀቱን በማጠናቀቅ ሁለተኛ ደረጃን አግኝታለች። ኬኒያዊቷ ጄሚማ ጄላጋት ውድድሩን በአሸናፊነት አጠናቃለች። ወደ አሜሪካ ቦስተን ያቀናው የኦሎምፒክ የ5 ሺህ ሜትር ብር ሜዳሊያ ባለቤቱ ኢትዮጵያዊው ደጀን ገብረመስቀል በ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ርቀቱን 13 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ አሸንፏል።
ደቡብ ኮሪያ ዴጉ ውስጥ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው ደበበ ቶሎሳ ርቀቱን 2:10፡23 በሆነ ጊዜ አጠናቆ ሶስተኛ ደረጃን አግኝቷል። ውድድሩን ከሁለት አመት በፊት ዜግነቱን ከኬኒያ ወደ ፈረንሳይ የቀየረው አብርሀም ኪፕሮቲች ሲያሸንፍ፣ ኬኒያዊው ቦኒፌስ ቩቢ ሁለተኛ ሆኗል። በሴቶቹ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ሙሉ ሰቦቃ ርቀቱን በ 2፡23፡43 በማጠናቀቅ ሁለተኛ ደረጃን አግኝታ አጠናቃለች። ውድድሩን ኬኒያዊቷ ማርጋሬት አካዪ አንደኛ በመውጣት አሸንፋለች።
በፍስሃ ተገኝ ቶታል433

No comments:
Post a Comment