Friday, April 12, 2013

ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የ2013 የአቤቶ አፍሪካ የሰላም ተሸላሚ ሆኑ

ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የ2013 የአቤቶ አፍሪካ የሰላም ተሸላሚ ሆኑ

     አቤቶ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ለኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ላበረከቱት ሙያዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አስተዋጽኦ የአመቱ ተሸላሚ አድርጓቸዋል፡፡ የአቤቶ ሊቀመንበር ሙሳና ሞሰስ በብሔራዊ ቤተመንግስት በተካሄደዉ የሽልማት ስነስርዓት ላይ “አቤቶ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የልማትና የሰላም ግንባታ ይገነዘባል፣ በዚህም የፕሬዚዳንቱን ሚና በማድነቅ ሽልማቱን ሰጥቷል” ብለዋል፡፡

    የተቋሙ ቦርድ ለዕጩዎች የአስተዋፆ ዘላቂነትና የአወንታዊ ተፅዕኖ መጠን ቅድሚያ ይሰጣል ያሉት የአቤቶ ሊቀመንበሩ ፕሬዚዳንት ግርማ ይህን ማሟላታቸዉን ተናግረዋል፡፡
ሊቀመንበሩ ሚስተር ሙሳና ሙሰስ እንዳሉት ፕሬዚዳንት ግርማ ለአካባቢ ጥበቃ ስራ ልዩ ትኩረት በመስጠታቸው በመስኩ ውጤት ተመዝግቧል፣ ይህም ለሌሎች የአፍሪካ መሪዎች አርአያ የሚሆን ነው፡፡
   "አልዎይስ ቢ ቶሌራንስ" አሊያም በምህፃረ ቃል አቤቶ የተሰኘው ድርጅት በአፍሪካ ለሠላም ግንባታ፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለማህበራዊ ልማት፣ ለዴሞክራሲና ለመልካም አስተዳደር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አፍሪካውያን ሽልማት የሚሰጥ ድርጅት ነው።
ድርጅቱ ከዚህ በፊት ለአፍሪካ ሰላም፣ እድገትና ልማት እንዲሁም ነጻነት አስተዋጽኦ ላበረከቱ እንደ ኔልሰን ማንዴላ፣ ዩዌሪ ሙሶቬኒ፣ ሳልቫ ኪርና ጁሌስ ኔሬሬ የሰላም ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment