Saturday, December 28, 2013

የቁልቢ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አመሠራረት

        ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ 461 ኪ/ሜ. ርቀት ላይ በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጋራ ሙለታ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ የዚህን ደብር አመሠራረት በተመለከተ በብዙ ሊቃውንት የሚተረከው የሚከተለው ነው፡፡ በዘጠነኛው መ/ክ/ዘ. ዮዲት ጉዲት ተነሥታ አብያተ ክርስቲያናትን ስትመዘብር፣ ክርስቲያኖችን ስትገድልና መጻሕፍትን ስትቆነጻጽል ንጉሥ አንበሣ ውድም በአኩስምና በአከባቢዋ የነበሩ ታቦታትንና ንዋያተ ቅዱሳትን በመያዝ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ዝዋይ መጣ፡፡ ከ40 ዓመታት ስደት በኋላ አንበሣ ውድም ወደ አኵሱም ሲመለስና የንዋያተ ቅዱሳት ቆጠራ ሲደረግ ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል በዝዋይ መቅረቱ ታወቀ፡፡
           
       ከኤርትራ ደብረ ሲና ማርያም የመጡና አባ ሌዊ የተባሉ አባት ታቦቱን ለማምጣት ከንጉሡ አስፈቅደው ወደ ዝዋይ መጡ፡፡ አባ ሌዊ ከሰባት ቀን ሱባኤ በኋላ ታቦተ ቅዱስ ገብርኤልን ይዘው ወደ አኵሱም ሲጓዙ ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ “እኔ ወደማሳይህ ቦታ ታቦቱን ይዘህ ሂድ” አላቸው፡፡ አባ ሌዊም ታቦቱን ይዘው ተከተሉት፡፡ በመጨረሻም ቁልቢ ደረሱ፡፡ ለአባ ሌዊም የተፈቀደላቸው ቦታ ይሄ መሆኑን ታቦቱም በኋላ ዘመን ለሕዝቡ ድንቅ ሥራ እንደሚሠራ ቅዱስ ገብርኤል ነግሯቸው ተሠወረ፡፡ አባ ሌዊ በቦታው ለ130 ዓመታት ያህል አገልግለው በንጉሥ ግርማ ሥዩም ዘመነ መንግሥተ ታኅሳስ 14 ቀን ዐርፈዋል፡
፡ 
   ግራኝ አሕመድ ኢትዮጵያን ሲወርር ብዙ ካህናት ከሰሜን ኢትዮጵያ ታቦታትንና ንዋያተ ቅዱሳትን ይዘው ሲጓዙ ቁልቢ ደረሱ፡፡ መልአከ ገነት መብረቁ፣ መምህር የማነ አብ፣ አባ ተከስተ ሥሉስ የተባሉ ካህናት ከተነጠፈ ድንጋይ ላይ የተጻፈ ነገር ያገኛሉ፡፡ ጽሑፉም ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል በሥዉር መቀመጡን፣ ልዩ ልዩ ተአምራት እንደሚፈጸምበት፣ ወደ ፊትም ታላቅ ቤተ መቅደስ እንደሚሠራበት፣ እንዴት አባ ሌዊ ታቦቱን ወደዚህ ቦታ እንዳመጡት የሚገልጽ ነበር፡፡ እነርሱም ይህን ታሪክ ይዘውት በነበረው መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ሕዳግ ላይ ጻፉት፡፡ ወደ ዝዋይ ደሴት ሲደርሱም መጽሐፉን በዚያ አኖሩት፡፡
      ልዑል ራስ መኰንን ከዝዋይ ደሴት መጽሐፈ ቀሌሜንጦስን አስመጥተው ሲያነቡ የቁልቢ ገብርኤልን ታሪክ በማግኘታቸው የቅዱስ ገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን ለማነጽ ተነሡ፡፡ ልዑል ራስ መኰንን በአከባቢው የአየር ንብረት ተማርከው በሥፍራው ቤት ሠርተው ነበር፡፡ ልዑል ራስ መኰንን ቁልቢ ገብርኤልን ከመትከላቸው በፊት ቦታው የአከባቢው ጎሳዎች የግጭት መነሃርያ ነበር፡፡ ሰላምን በአከባቢው ከመሠረትህ በቦታው በስምህ ቤተ ክርስቲያን እሠራልሃልሁ ብለው እንደተሳሉም ይነገራል፡፡

        የተሳሉት በመፈጸሙ የቅዱስ ገብርኤል ታቦት የት እንዳለ ሲያፈላልጉ ቡልጋ ውስጥ ከአዠጉጉ ካህናተ ሰማይ ጋር አባ ዱባለ የተባሉ ካህን ያስቀመጡት ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል መኖሩ ተነገራቸው፡፡ ልዑል ራስ መኰንን ለአባ ዱባለ መልእክት ስለላኩባቸው ከሐረር በተላኩ ካህናት አማካኝነት የቅዱስ ገብርኤልን ታቦት ላኩ፡፡ ልዑል ራስ መኰንንም ከነሠራዊቶቻቸው ሸንኮራ ድረስ ሄደው ታቦቱን በመቀበል የካቲት 21 ቀን 1884 ዓ.ም ታቦቱ ቁልቢ ገባ፡፡ የመቃኞው ሥራ በ1883 ዓ.ም ተጀምሮ ፍጻሜ አግኝቶ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረው ሐምሌ 19 ቀን 1884 ዓ.ም ነው፡፡ 
   
  በዚሁ ዕለት የዋናው ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ሥራ የመሠረቱ ድንጋይ ተጥሎ ታኅሳስ 19 ቀን 1888 ዓ.ም የቤተ ክርስቲያኑ ሥራ ተፈጽሞ በአቡነ ማትያስ ተባረከ፡፡ ቦታውን ከባለ አባቶች የገዙት በአርባ የቁም ከብት ነው፡፡ ራስ መኰንን መጋቢት ዘጠኝ ቀን 1889 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ሲሄዱ እዚህ ቦታ ላይ በድንገት ስለታመሙ በዕለቱ ሥጋወደሙ ተቀብለውበታል፡፡ በመጀመርያ ሲተከል በገጠር ቤተ ክርስቲያን ሥሪት ሲሆን በኋላ ግን በስእለት ሰማኢነቱ በመላ ኢትዮጵያ እየታወቀ ስለ መጣ ደብር ሆኗል፡፡
                            
  የቅዱስ ገብርኤል ምልጃና በረከት አይለየን!!

                                                 (ምንጭ፡ የቤተ ክርሰቲያን መረጃዎች- በዲ/ን ዳንኤል ክብረት)

Bethlehem Tilahun Alemu named to 20 Powerful Women of 2013 alongside Angelina Jolie, Oprah Winfrey , Hilary Clinton and others.


   Ethiopian entrepreneur Bethlehem Tilahun Alemu is one of Africa’s most successful women. She built SoleRebels, a shoe company that pays fair wages to its employees and uses locally sourced materials such as organic, hand-spun cotton.

 

  She was able to turn SoleRebels it into an internationally recognized brand: the shoes have been carried in Urban Outfitters and Whole Foods, and this year, Alemu will open stand-alone boutiques in Germany and Sweden. SoleRebels has become a hugely successful, sustainable, truly world-class enterprise.

    This has been an exciting year for women. We are finally working together to shift women’s roles in society not by compromising our femininity, but by using our true qualities to make real changes in the workplace, in our communities and in the world. It’s been especially gratifying knowing that we, Emerging Women, participated in generating change.

   
  I am so inspired by all the women that passionately and courageously are creating a new life for themselves, one that is fully expressed and supported by the truth of who we are.

   Change for women today is palpable. It is so important that we take meaningful action when called to participate in this movement. We are more ambitious, more daring, more unified and more determined to create impact by following our true calling, by speaking up, by crossing barriers, by unlearning habits, by being vulnerable, by welcoming failure as part of success and by expressing our true feminine power.

     And even though there is a lot more to accomplish and fight for, we want to celebrate the women who inspire and motivate us. You’ll find below a list of 20 trailblazers from different industries and different parts of the world who are creating change in the world.
  

And don’t forget, if you are committed to expressing your unique gifts to the world, you’ll find a community of like-minded women ready to help you succeed at Emerging Women Live. Also, we are curious to know who inspired you this year, so please leave a comment below and share with us the women that motivate you to create real change in the world.

                                                Source: emergingwomen.com

Thursday, December 26, 2013

ሳክስፎኒስት ቴዎድሮስ ምትኩ - በጌጡ ተመስገን

‹‹ቦብ ማርሌይ ጊዮን ሆቴል ሲዋኝም፤ ሙዚቃ አድምጦ ሲወጣ ልብ ያለው ሰው አልነበረም›› የቦብ ማርሌይ “No woman, No cry” ‹‹ ውማን ክርይ›› የተሰኘውን ዘፈን ሙሉቀን መለሠ ከሪዳ ኢብራሂም ጋር በጊዮን ሆቴል ክለብ ይጫወቱት ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ ቦብ ማርሌይ ኢትዮጵያ መጥቷል፡፡ ቦብ ማርሌይ እነሙሉቀን ሲጫወቱ ተመልካች ሆኗል፡፡ (እነርሱም) ቦብ ማርሌይ በክለብ ውስጥ ተገኝቶ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ያጣጥማል፤ ይመሰጣል ብለው አልጠበቁም፡፡
  አንድ እንግዳ ሰው - ለመዝፈን ባንዱን ፈቃድ ጠየቀ፡፡ ተፈቀደለት፡፡ ጃማይካዊው እንግዳ ሲዘፍን ድምፁን የሚያውቁት ዓለም አቀፍ አርቲስት ቦብ ማርሌይ እንደሆነ አወቁ፡፡ በዚያን ወቅት በጊዮን ሆቴል ክለብ ውስጥ ሲጫወቱ የነበሩት ሙሉቀን መለሠ፣ ሪዳ ኢብራሂም፣ አበራ ፈይሣ፣ ዳዊት ካሣ፣ ጥላዬ ገብሬ፣ ሽመልስ በየነና ተስፋዬ ተሠማ ነበሩ… (ይሁን እንጂ ቦብ ማርሌይ ጊዮን ሲዋኝም፤ ሙዚቃ አድምጦ ሲወጣ ልብ ያለው ሰው አልነበረም) ቦብ ማርሌይ የሙሉቀን መለሠ ችሎታን አደነቀ፡፡

   ‹‹ሻሸመኔ›› የተሰኘ አልበም ለመሥራት ተስማሙ፡፡ ቦብ ማርሌይ ለሙሉቀን ግጥሞች ሠጥቶት ወደ ጃማይካ ሄደ፡፡ ከዚያም ሙሉቀን የዘፈኖቹን ግጥም ማጥናት ጀመረ፡፡ ይሁን እንጂ የቦብ ማርሌይ ዜና እረፍቱ ተሰማ፡፡ ሳክስፎኒስት ቴዎድሮስ ምትኩ - ያጫወተኝን ታሪክ ነበር
   
    ቴዎድሮስ የሙዚቀኛው Teshome Mitiku ታላቅ ወንድም ነው፡፡ (የቀበና ልጆች) … (ETHIOPIAN LEGEND: Teshome Mitiku Singer and songwriter ‘’Gara Sir New Betesh – Mot Adeladlogn – Yezemed Yebada - Yemekabir Echognaye – SUSEGNASH - Hasabe - etc’’ … his famous daughter, the Swedish Emilia and his brother, saxophonist Tewodros Mitiku (በነገራችን ላይ ተሾመ ምትኩ ከኢትዮጵያ ከወጣ 40 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል) … ሳክስፎኒስት ቴዎድሮስ ምትኩ (30ዓመት በፊት) .. 1983 ወደ አሜሪካ ቴክሳስ ግዛት አመራ፡፡
    
   
   እ.. 2007 ኢትዮ - አሊያንስ ፍራንሴዝ ታዋቂው ግርማ በየነን እና ሦስት ዝነኛ ሳክስፎኒስቶች ጥላዬ ገብሬ፣ ቴዎድሮስ ምትኩና ሞገስ ሀብቴን አምጥተዋቸው ነበር፡፡ የእነርሱ የማይጠገበው የሙዚቃ ሥራ እንዲሁም (የህዝቡ ፍቅርና አድናቆት ምላሽ) በቦታው የነበረ ሰው የሚረሳው አይደለም፡፡ ሁለት በመሣሪያ የተቀነባበሩ ምርጥ ሥራዎችን በካሴትአበርክቶልናል፡፡ የሳክስፎኒስት ቴዎድሮስ ምትኩ ባለቤት (የጥላሁን ገሠሠ ባለቤት ሮማን በዙ) እህት ስትሆን፤ ከማዕዛ በዙ ጋር 22 ዓመታት በትዳር ዓለም ቆይተዋል። ቴዎድሮስ ምትኩ ባደረበት ህመም በሜሪላንድ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ አርፏል፡፡ (ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበርየሳክስፎኒስት ቴዎድሮስ ምትኩ - አማሌሌ - የሙዚቃ ሥራውንአድምጡ፡፡                      
                                   http://youtu.be/xbRnPCmnutw 
                                                     
   
 እ.. 2014 ኢትዮጵያን የሚወክሉ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኞችንና ረዳት ዳኞችን ስም ዝርዝር አሳወቀ፡፡

  አለም አቀፉ የእግር ካስ የበላይ ፊፋ /FIFA/ .. 2014  የውድድር ዘመን ኢትዮጵያን የሚወክሉ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኞችንና ረዳት ዳኞችን ስም ዝርዝር አሳወቀ፡፡ ኢትዮጵያ 4  ወንድ ዳኞች 2 ሴት ዳኞች 3  ረዳት ሴት ዳኞች  እንዲሁም  7 ወንድ ረዳት ዳኛ ተመርጠዋል፡፡


ወንድ ዋና ዳኞች ሴት ዋና ዳኞች 

1.
ኃይለየሱስ ባዘዘው
2.
ጽጌ ሲሣይ
3.
ለሚ ንጉሴ
4.
ሊዲያ ታፈሰ
5.
በላይ ታደሰ
6.
ባምላክ ተሰማ
ወንድ ረዳት ዳኞች ሴት ረዳት ዳኞች
1. ትግል ግዛው
2.
ትርሀስ /ዮሐንስ
3.
ክንዴ ሙሴ
4.
ወይንሸት አበራ
5.
ተመስገን ሣሙኤል
6.
ወጋየሁ ዘውዱ
7.
ሸዋንግዛው ተባባል
8.
ኃይለራጉኤል ወልዳይ
9.
በላቸው ይታየው
10.
ክንፈ ይልማ

የኢትዮጵያ እግር ካስ ፌዴሬሽንም ለዳኞቹ እንካን ደስ አላችሁ ብሏል፡፡

                                                                                      ምንጭ ፡- ድሬ ቲዩብ