Wednesday, June 19, 2013

ብሔራዊ ቡድኑ 3 ነጥብ ጎልና 6 ሺ የስዊስ ፈራንክ ይቀጣል

 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተገቢ ያልሆነ ተጫዋች በማሰለፉ የሚቀጣው 3 ነጥብ ጎልና 6000 የስዊስ ፈራንክ ብቻ መሆኑን የኢትዮጰያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

   ቦትስዋና ከኢትዮጵያ ባደረገችው ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡደን 2 ለ 1 ያሸነፈበት ውጤት ብቻ እንደሚሰረዝና 3 ነጥብ ለቦትስዋና እንደሚሰጥ የፊፋ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ማሳወቁን የኢትዮጰያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አረጋግጧል፡፡

    ስለሆነም ኢትዮጵያ ደቡብ አፍሪካን 2 ለ 1 ያሸነፈችበት ውጤት የሚፀና ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምድቡን በ10 ነጥብ እየመራ የሴንትራል አፍሪካውን ጨዋታ ይጠባበቃል፡፡በዚህ መሰረትም ኢትዮጵያ በ10 ነጥብና 2 ንፁህ ጎል ስትመራ ደቡብ አፍሪካ በ8 ነጥብና 4 ንፁህ ጎል ትከተላለች፡፡ ቦትስዋና በ7 ነጥብና ያለምንም ግብ ክፍያ 3ኛ ስትሆን ማዕከላዊ አፍሪካ በ3 ነጥብ 6 የግብ እዳ በመጨረሻው ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

No comments:

Post a Comment