Saturday, June 8, 2013

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 166 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ

     ከተመረቁት መካከል 36ቱ ሴቶች ሲሆኑ ይህም ሃገሪቱ በጤናው ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎና የምዕተ አመቱን የልማት ግብ ለማሳካት የምታደርገውን እንቅስቃሴ የሚያጠናክር መሆኑ በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ ተገልጧል፡፡በስነ ስርዓቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔና የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ካሳ ተክለብርሃን እንዳሉት ኢትዮጵያ የጤናውን ዘርፍ ልማት ለማሳደግ በጀመረችው ጉዞ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የህክምና ባለሙያዎችን ለማፍራት እየሰራች ነው፡፡
 
    “ተመራቂዎች በጤናው ዘርፍ የተገኙ ድሎችን ቀጣይነት ለመድገም በስነ ምግባር ታንፃችሁ ሃገሪቱንና ህዝቦቿን ማገልገል ይኖርባችኋል” ብለዋል አቶ ካሳ ተክለብርሃን ፡፡ ጤናው የተጠበቀ አምራች ዜጋ ለማፍራትና መንግስት ለከፍተኛ ትምህርት በሰጠው ልዩ ትኩረት ኮሌጁ ከአመት ወደ አመት የቅበላ አቀቅሙን እያሳደገ መምጣቱን የገለፁት ደግሞ የዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አድማሱ ፀጋዬ ናቸው፡፡
 
      ተመራቂ ዶክተሮች ግንባር ቀደም የጤና ሰራዊት ሆነው ወደተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች በመሄድ የጤናው ሽፋን የማሳደግ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል፡፡
ተመራቂዎችም የሙያውን ስነ ምግባር ጠብቀው ሃላፊነታቸውን ለመወጣትና ህዝቡን በላቀ ተነሳሽነት ለማገልገል መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡

No comments:

Post a Comment