Tuesday, June 18, 2013

በኦስሎ የዳይመንድ ሊግ ውደድር መሰረት ደፋር በ5 ሺ ሜትር አሸነፈች

      በኖዌይ ኦስሎ የዳይመንድ ሊግ ውደድር መሰረተ ደፋር በ5 ሺ ሜትር አሸነፈች፡፡
የመሰረት ደፋር እና ገንዘቤ ዲባባን ፉክክር ጨምሮ 5 ኢትዮጵያውያን ያሳተፈው የ5 ሺ ሜትር በመሰረት የበላይነት ተጠናቋል፡፡

    መሰረት የገባችበት 14፡26፡90 የአመቱ ፈጣን ሰአት ሆኗል፡፡ በዚህም  መሰረት ደፋር በ 6 ነጥብ የዳይመንድ ሊግ የ5 ሺ ሜትር ፉክክሩን  በአንደኝነት መምራት ጀምራለች፡፡ገንዘቤ ዲባባ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቃለች፡፡ ኬንያዊቷ ቪዬላ ጂላጋት 2ኛ ወጥታለች፡፡
ቡዜ ድሪባ 6ኛ፣ ገነት ያለው 12፣ጎይቶቶም ገብረስላሴ 13ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡

      በ8 መቶ ሜትር ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ወድድር የተመለሰቸው ፋንቱ መረሶ 4ኛ ደረጃን በመያዝ ፈፅማለች፡፡ በ1ሺ 5 መቶ ሜትር ሴቶች አክሱማይት አምባዬ 2ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቃለች፡፡ ስዊዲናዊቷ ምእራፍ ባህታ  በርቀቱ ቀዳሚ ሆናለች፡፡ በ3ሺ ሜትር መሰናክል ሮባ ጋሪ 7 ኛ ሆኗል፡፡ኪፕራቶ በርቀቱ አሸንፏል፡፡በ 2 መቶ ሜትር ዩዚየን ቦልት 19፡79፡60 ሰዓት በመግባት የቦታውን እና የአመቱን ፈጣን ሰዓት በማሻሻል አሸንፏል፡፡
ቀጣይ የዳይመንድ ሊግ ፉክክር በእንግሊዝ በርማንግሀም ይካሄዳል፡፡

No comments:

Post a Comment