Friday, June 14, 2013

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የብቃት ደህንነት ተሸላሚ ሆነ


     በአፍሪካ ፈጣኑና እያደገ ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2013 የብቃት ደህንነት ለሶስተኛ ጊዜ ከቦምባርዴር ተሸላሚ መሆኑን አየር መንገዱ ገልጿል፡፡
    ሽልማቱ ለአየር መንገዱ የተሰጠው ለተጓዦች በአማካይ 99 በመቶ በሚያደርሰው መረጃ እና በ2012 ከተጓዦች በሰበሰበው የገቢ መጠን እንዲሁም በአጠቃላይ አየር መንገዱ በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ በሚያደርገው ቀልጣፋ የደንበኞች አገልግሎት ስራ ነው፡፡
በስነስርአቱ ላይ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም እንዳሉት ፥ ሽልማቱ  በየቀኑ እያሻሻልን ላለነው የደንበኞች አገልግሎት ቀጣይነት እንዲኖረው የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡ አየር መንገዱ በአሁኑ ሰአት 13 Q-400 አውሮፕላኖችን የሚጠቀም ሲሆን ፥ ይህም ሰፊ አካባቢያዊ የበረራ መስመሮችን በመሸፈን በቱሪዝምና ንግድ እንቅስቃሴ ለሚጓዙ ደንበኞች በበቂ ሁኔታ ፍላጎታቸውን ለማማሟላት እንደሚያስችለው ነው የተገለጸው፡፡
    አየር መንገዱ በQ-400 አውሮፕላኖች በአገር ውስጥ ከሚያካሂደው አስራ ሰባት የበረራ መስመሮች በተጨማሪ በጅቡቲ፣ ሞምባሳ፣ ናይሮቢ፣ ኪሊማንጃሮ፣ ዳሬሰላም፣ ዛንዚባር፣ ኪጋሊ፣ ጁባ፣ ካርቱም፣ በርበራ እና ኢንቴቤ እየተጠቀመ ነው፡፡እ.ኤ.አ በ1946 የመጀመሪያውን አለም አቀፍ በረራ ወደ ካይሮ በማድረግ ስራውን የጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአራት አህጉሮች በ72 አለምአቀፍ የበረራ መዳረሻዎች ላይ እየሰራ ይገኛል፡፡

                                                    ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

No comments:

Post a Comment