Monday, June 17, 2013

ፊፋ በሶስት የአፍሪካ አገራት ላይ ማጣራት ሊያደርግ ነው


    አለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፊፋ) በሶስት የአፍሪካ አገራት ላይ ማጣራት ሊያደርግ ነው።
ማጣራት የሚደረግባቸው አገራት ኢትዮጵያ ፣ ቶጎ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ሲሆኑ ፥ አገራቱ በ2014ቱ የብራዚል አለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች የአለም አቀፉ የእግር ኳሰ ማህበር ህግን በጣሰ መልኩ ተጫዋቾችን አሰልፈዋል በሚል ነው ።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ማጣራት የሚደረግበት ከቦትስዋና አቻው ጋር ጋቦሮኒ ላይ ባደረገው ጨዋታ ላይ ሁለት የማስጠንቀቂያ ካርድ ያየውን ምንያህል ተሾመን በመጠቀሙ ነው። በሚደረገው የማጣራት ሂደት ጉዳዩ እውነት ሆኖ ከተገኘ ዋልያዎቹ የ3 ነጥብ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ፊፋ በመግለጫው አስታውቋል።

     በተመሳሳይ የቶጎ ብሄራዊ ቡድን ከካሜሮን አቻው ፥ እንዲሁም የኢኳቶሪያል ጊኒ ቡድን ከ ኬፕቨርዴ አቻው ጋር ሲጫወቱ ተመሳሳይ ጥፋት በመፈጸማቸው ፊፋ በአገራቱ ላይ ምርመራውን ያደርጋል።
         ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ ባደረግናቸው አምስት ጨዋታዎች ላይ ከኢትዮጵያ በኩል ቢጫ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋችን ስም ዝርዘር ከፊፋ ድረገጽ በተገኘው መሰረት ከታች ቀርቧል።  እንደመረጃው ከሆነ ምንያህል ሁለት ቢጫ ካርድ ማየቱ እርግጥ ይመስላል። በነገራችን ላይ በረኛው ጀማል ጣሰው እና አይናለም ሃይሉ ትናንት ከደቡብ አፍሪካ ጋር ባደርግነው ጨዋታ ሁለተኛ ቢጫ ካርዳቸውን ያገኙ በመሆኑ በቀጣዩ ከሴንትራል አፍሪካ ጋር ባለን ወሳኝ ጨዋታ ላይ መሰለፍ አይችሉም።

1) June 3 2012 South Africa 1-1 ethiopia
~Sisay Bancha
~Abebaw Butako
~Minyahile Teshome BEYENE
~Addis Hintsa

2) June 10, 2012 Ethiopia 2-0 Central Africa
~Seyoum Tesfaye

3) March 24, 2013 Ethiopia 1-0 Botswana
~Jemal Tasew
~ Menyahile Teshome Beyene

4) June 8, Botswana 1-2 Ethiopia
~ Aynalem Hailu
~ Asrat Megersa Gobena

5) June 16, Ethiopia 2-1 South Africa
~Jemal Tasew
~Aynalem Hailu

ምንጭ     http://www.fifa.com      , DireSport

No comments:

Post a Comment