ለ2006 154 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ተዘጋጀ
በዚህ መሰረት ለ2006 በጀት አመት በፌዴራል መንግስት ለሚከናወኑ ስራዎችና አገልግሎቶች የሚያስፈልገውን በጀት አጽድቆ በበጀት አመቱ መጀመሪያ ወቅት ስራ ላይ ማዋል አስፈላጊ በመሆኑ እና የፌዴራሽን ም/ቤት በወሰነው ቀመር መሰረት የፌዴራሉ መንግት ለክልሎች የሚሰጠውን የድጋፍ በጀት መጠን መወሰን ስለሚኖርበት ከሐምሌ 1 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2006 ዓ.ም በሚፈጸመው በአንድ የበጀት አመት ጊዜ ውስጥ የፌዴራል መንግስት በጀት 154,903,290,899/ አንድ መቶ ሃምሳ አራት ቢሊዮን ዘጠኝ መቶ ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር/ እንዲሆን ወስኗል፡፡
ከዚህ ውስጥ፡-
· ለመደበኛ ወጪዎች--------------------ብር 32,530,000
· ለካፒታል ወጪዎች ------------------- ብር 64,321,732,351
· ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ --------------- ብር 43,051,558,548
· የምዕተ ዓመቱን ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ-- ብር 15,000,000,000 እንዲሆን ተመድቧል፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በቀረበው ረቂቅ በጀት ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አስተላልፏል፡፡
No comments:
Post a Comment