Saturday, March 23, 2013


 በቱር ደ ታይዋን የብስክሌት ውድድር ኢትዮጵያዊው ፅጋቡ ገ/ማሪያም ግርማይ አንደኛ ወጣ

    በቱር ደ ታይዋን የብስክሌት ውድድር ኢትዮጵያዊው ፅጋቡ ገ/ማሪያም ግርማይ አንደኛ ወጣ


        በታይዋን እየተካሄደ ያለው 25ኛው የቱር ደ ታይዋን የብስክሌት ውድድር ኢትዮጵያዊው ፅጋቡ ገ/ማሪያም ግርማይ በአምስተኛው ዙር አንደኛ ወጣ፡፡መጋቢት 13/2005ዓ.ም በተካሄደውን 144 ኪሎ ሜትር የሸፈነው 5ኛው ዙር የቱር ደ ታይዋን ፅጋቡ ገ/ማሪያም ግርማይ አንደኛ የወጣው ርቀቱን 2 ሰአት 59 ነጥብ 35 ደቂቃ በማጠናቀቁ  ነው፡፡
          ኢትዮጵያዊ ብስክሌተኛ ፅጋቡ ገ/ማሪያም በውድድሩ አንደኛ መውጣቱ ለሀገሩና ለአፍሪካ ትልቅ ድል መሆኑን ገልጿል፡፡ ብስክሌተኛ ፅጋቡ እስከ አሁን በተካሄዱት አምስት ዙር የቱር ደ ታይዋን ውድድር በድምር ውጤት በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

No comments:

Post a Comment