Friday, March 29, 2013

ሁለት እጅ አልባዋ አብራሪ ጄሲካ ሰኞ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልምዷን ታካፍላለች


አሜሪካዊቷ ሁለት እጅ አልባዋ አውሮፕላን አብራሪ ጄሲካ ኮክስ ቻምቤሌይን የፊታችን ሰኞ 23/2005 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ንግግር ታደርጋለች፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እንደገለፀው በተፈጥሮ ሁለት እጆቿን ያጣችው የ32 አመት ወጣት በዩኒቨርስቲ ለ300 ተማሪዎቸ መጋቢት 23 ቀን 2005 ንግግር ታደርግላቸዋለች፡፡
  በቀስቃሽ ንግግሮቿ የምትታወቀው ጄሲካ ወደ ኢትዮጵያ የምትመጣው ሀንዲካፕ አለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅትና በአሜሪካ አለም የልማት ተራድኦ ድርጅት/ ዩ ኤስ አይ ዲ/ ትብብር ነው፡፡ ጄሲካ በመላው አለም የምትታወቅበት እጆች ሳይኖሯት አውሮፕላን ለማብረር የምትችልና ለዚህም የአብራሪነት ፈቃድ በማግኘቷ ነው፡፡

በአሪዞና ግዛት ተሰከን የተወለደችው ጄሲካ ከጽንስ ጀምሮ እጆቿ የእግርንም ባህርይ ይዘው በመወለዷ ለምታከናውናቸው ተግባራት ችግር እንደማይፈጥርባት መረጃዎች ያመለከታሉ፡፡ በዚህም የምትፈልገውን ሁሉ በእግሮቿ ለማድረግ እምብዛም አትቸገርም፡፡ሀንዲካፕም አለም አቀፍ አካል ጉዳተኛ ህጻናት ከትምህርት እንዳይገለሉ በሚደረገው ጥረት አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑንም መግለጫው አመልክቷል፡፡

No comments:

Post a Comment