የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት የመረጃ ቅብብሎሽን በጥራትና በቅልጥፍና ለማሰራጨት የሚያስችለውን ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ህንጻና የሚዲያ ቴክኖሎጂ አስመረቀ። በኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የትምህርት ሚንስትር ተመርቆ ተከፈፍቷል ። በባህርዳር ከተማ የተገነባው ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ህንጻና የሚዲያ ቴክኖሎጂ ባለ አራት ፎቅ ሲሆን በዉስጡም ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎችን አካቶ የያዘ ነዉ ።
የሚዲያ ኮምፕሌክሱን የመረቁት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የትምህርት ሚንስትሩ አቶ ደመቀ መኮነን እንደገለጹት የሚዲያ ኮምፕሌክስ ህንጻው ዘመናዊ የሚዲያ መሰረተ ልማትን ሙሉ በሙሉ ያሟላ በመሆኑ ለክልሉ ህዝብና መንግስት የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው ። ህንፃው ሁለት ዘመናዊ መሳሪያ የተገጠሙላቸው የቴሌቪዥን ስቱዲዮዎችን ጨምሮ የቴሌቪዥንና የሬድዮ ስርጭትና የህትመት ስራዎች የሚከናወኑባቸው የዘመናዊ ቴክኖሎጅ መሳሪያዎች የተሟላለት ነው።
በተለይም ድርጅቱ በራሱ ስቱዲዮ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭትን አሁን ካለበት በቀን የአንድ ሰዓት ስርጭት በራሱ ቻናል ወደ 24 ሰዓት፣ ፣የመደበኛ ሬድዮ ፕሮግራሙን ወደ 18 ሰዓት እንዲሁም የባህርዳርና ሌሎች የኤፍኤም ሬድዮ ስርጭትን ወደ 24 ሰዓት ለማሳደግ እንደሚያስችለው በምረቃው ላይ ተገልጿል።
No comments:
Post a Comment