በትግራይ ክልል የህጻናትና እናቶችን ሞት መቀነስን ጨምሮ በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙ ግንባር ቀደም ሰራተኛ በመሆን የተመረጠችዉ ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ትርሀስ መብራቱ ትናንት አለም አቀፍ ሽልማት ተቀበለች ። የመጀመሪያዉን የቢልና ሚሊንዳ ጌትስ አለም አቀፍ ሽልማት ወጣቷ ልታሸነፍ የቻለችዉ በአድዋ ወረዳ ሶሎዳ ጤና ኬላ በህብረተሰብ የጤና አገልግሎት በባረከተችዉ መልካም አስተዋጽኦ ነዉ ። ወጣቷ በአካባቢዋ የሚገኙ ነፍሰጡር እናቶች በጤና ተቋሙ እንዲወልዱ በማድረግ ፣16ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሞች በስራ በመተርጎም ለዉድድር ቀረቡት ከ35 አገሮች የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች መካከል በግንባር ቀደምትነት ተመርጣ ለሽልማት መብቃቷን የጥምረቱ ሊቀ መንበር አስታዉቀዋል ።
በተጨማሪ የወባ ፣ የብላሃርዚያና የአተት በሽታዎችን በመቆጣጠርና ስለ አመጋገብ ስርአት ህብረተሰቡን በማስተማር ፣ የጤና ሰራዊት መገንባት ካከናወነቻቸዉ ተግባራት መካከል ተጠቃሽ መሆናቸዉን ተናግረዋል ። በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጤና ኤከስቴንሽንና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ በቀለ በስነ ስርአቱ ላይ እንደተናገሩት ፥ ለወጣቷ የጤና አገልግሎት ሰራተኛ የተበረከተዉ አለም አቀፍ ሽልማት በመላ ሀገሪቱ በጤና ኤክስቴንሽን ፕርግራም የተሰማሩትን ሰራተኞች ለበለጠ ስራ የሚያተጋ ነዉ ።
ኢትዮጵያዊቷ የጤና አገልግሎት ሰራተኛ ትርሀስ መብራቱ ያገኘቸዉ አለም አቀፍ ሽልማት የጤና ፖሊሰዉን ዉጤታማነትና የመንግስትን ጥረት ጭምር የሚያሳይ ነዉ ብለዋል ። በሽልማት ስነስረአቱ ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊዎች ፣ የቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋዉንዴሽን ተወካዮችና የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተወካዮች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል ።
No comments:
Post a Comment