Friday, March 1, 2013

የግጥም ስብስቦች.....


    መሸ ደግሞ አምባ ልውጣ!

አምባ ወጥቼ እኩለ-ሌት ስለት ገብቼ በስሟ
ከርሞ ሰይጣን በሷ አስቶኝ፤ ልገላገል ከህመሟ
ጠበሏ አፋፍ በጨረቃ፤ ደጋግሜ፤ ማህሌት ቆሜ
ሆዴ ቃትቶ ባር ባር ብሎ፤እርቃኔን ከሷ ታድሜ
ደጀ ሰላሟን በአራት እግር፤ ተንበርክኬ ተሳልሜ
በስጋዬ እሚነደውን፤ በጸሎት ላቤ አጣጥሜ
እፎይ ብዬ አመስግኜ፤ ውዳሴዋን ደጋግሜ...
ገና ከደጅዋ እልፍ ሳልል፤ ደሞ ይምጣ የቁም ህልሜ?
ሌት በጥምቀቷ የነጣው፤ ነጋ፤ ደፈረሰ ደሜ።
ለሷ እንጂ ለኔ አልያዘልኝ፤ አዬ የስለት አታምጣ!
በውጣ ውረድ በጠበል፤ ባሣር ወዜ ቢገረጣ
ልክፍቷ እንደሁ አልለቀቀኝ፤ መሸ ደሞ አምባ ልውጣ!

                                    /ሎሬት ጸጋዬ /መድሀን፣ እሳት ወይ አበባ!/


                  መሆን አለመሆን

በመሆን እና ባለመሆን
በማድረግ እና ባለማድረግ
በሁለት ታዛዦች ስር መውደቅ ነው
ሰው የመሆን ትልቅ ህግ
ሊኖሩት በማይፈቅዱት ህግ 
ሊፈጽሙት በማይሹት ስህተት
በጣምራ ግጭቶች መሃል መቆም ነው ሰው የመሆን ሰውነት
ይሄ ሁሉ ፍጡር ይሄ ሁሉ ፍጡር 
በፍጥረት መድረክ ላይ የሚርመሰመሰው
ላንዲት ቅጽበት እንካን ሰው ሆኖ አያውቅም ሰው ሊሆን ጽንስ ነው
ሰው እስኪሆን ድረስ አንዳንድ ጊዜ አምላክ አንዳንዴ ሰይጣን ነው።
                                      
                                                 /ሎሬት ፀጋዬ /መድህን/

              መሄዴ ነው

ባር ባር አለው ሆዴ ልቤ መሬት ለቆ
ሊያከንፈኝ እንዳይሆን አለግብሩ መጥቆ
አለአስተዳደጉ አለባህሉ ወድቆ
ሽው እልም ሽው እልም ልቤ ወፌ ይላላ
በመስተፋቅር ቀስት በሮሮ ምህላ
እንደደመና አክናፍ እንደጮራው ጥላ
ሽው እልም ሽው እልም ሽው እልም ይላላ
ነሸጠው ሸፈጠ ሄደ ሸመጠጠ
በመስተፋቅር ቀስት በሮሮ አመለጠ።
                                
                                       /ሎሬት ፀጋዬ /መድህን/

            ክልክል ነው

ማጨስ ክልክል ነው
ማፍዋጨት ክልክል ነው 
መሽናት ክልክል ነው
ግድግዳው በሙሉ ተሰርቶ በክልክል 
የቱ ነው ትክክል? 
ትንሽ ግድግዳና ትንሽ ኃይል ባደለኝ 
"
መከልከል ክልክል ነው" የሚል ትዕዛዝ አለኝ፡፡
                              (በእውቀቱ ስዩም፣ የ፣ሣት ዳር ሐሳቦች፣ 2000)

          «በጠራ ጨረቃ»

በጠራ ጨረቃ በእኩለ ሌሊት
አይኖቿ እያበሩ እንደ ከዋክብት
«
ሳማት ! ሳማትአሉት
«
እቀፍ ! እቀፋት።»
አላወላወለም ወጣቱ ታዘዘ
ወገቧን አንገቷን እጇን በእጁ ያዘ
ምንም እንኳ ጡቷ እንደሾህ ቢዋጋ
ጣቷ በመሆኑ የጉማሬ አለንጋ
ጆሮ ግንዱን ሰማው በጥፊ ሲናጋ።
ጀማሪ መሆን ! ተማሪነት
ትእዛዝ መፈጸም ምክር መስማት !
በጠራ ጨረቃ በኩለ ሌሊት...       
                      /ከመንግስቱ ለማ /

        ወሰደው ከፊትዋ

ልጅነት ሆነና ዕረፍት የሌለበት 
አንገት ያለሃሳብ የሚመዘዝበት
ልብ ከግንባር ላይ የሚነበብበት
ለጋነት ባጠራው ይሉኝታ ቢስ ፊትዋ 
በስልት ያልተገራው ግልጽ አስተያየትዋ
መልሶ ቢያሳየው የራሱን አንካሳ 
የባህሉን ጅራፍ የወጉን ጠባሳ 
ምነው ዓይን በላች ይሉኝታ አጣችሳ”“
እያለ ጮኸና ልቧን አስበርግጐ
ወሰደው ከፊትዋ ልጅነትዋን ጠርጐ 
በሞረድ ምላሱ ፈግፍጐ ፈግፍጐ . . . 
                               
(ታገል ሠይፉ፣ ቀፎውን አትንኩት፣ 1986)
       ጠላቴን ስመርቅ 

በስልጣን ከፍ ከፍ
በዝና ከፍ ከፍ
በሀብትም ከፍ ከፍ
ወደላይ ከፍ ከፍ
ከፍ ከፍ.... ከፍ ከፍ
ከዛ የወደቅህ ዕለት አጥንትህ እንዳይተርፍ::


                               /ገጣሚ ታገል ሰይፉ/

 ደመወዙን ቢጥል
አንስተው ጠጡበት
ባርኔጣውን ቢጥል
ወስደው ደመቁበት
ከዘራውን ቢጥል
ተመረኮዙበት
በሄደበት ሁሉ 
እየተከተሉ
በጣለው ሲያጌጡ
በጣለው ሲያተርፉ
ራሱን ሲጥል ግን
አይተውት አለፉ……            
                 
                          በውቀቱ ስዩም  (ካንድምታ ላይ የተወሰደ )

     ፍቅር ጥላ ሲጥል

በገና ቢቃኙ፡
ሸክላ ቢያዘፍኑ
ክራር ቢጫወቱ፡
ለሚወዱት ምነው
ሙዚቃ ቢመቱ
ቢቀኙ ቢያዜሙ
ቃል ቢደረድሩ
ጌጥ ውበት ቢፈጥሩ
ቤት ንብረት ቢሠሩ
አበባ ቢልኩ
ደብዳቤ ቢልኩ
ምነው
ቢናፍቁ !
አገር ቢያቋርጡ
ቢሔዱ ቢርቁ
ዓመት ቢጠብቁ
ዘመን ቢጠብቁ።
ለሚወዱት ምነው ....

              /ገብረ ክርስቶስ ደስታ 1998 96-97/
            
       እውነት ለፈለገ....

ፀሀይ ስትገባ
ጥያቄ ይወጣል ፀሀይን ተክቶ
ልቤም እስከንጋት ያልፈዋል ተኝቶ
ግድ ነው በለሊት አዳፍኖ ማለፉ
እሳትን ባመድ ሆድ ጥያቄን በን'ቅልፉ
ከጎረምሶች ከንፈር ጪስ እየነጠቀ
ከኮረዶች ጡት ላይ ሽቶ እየሰረቀ
ነፋሱ ይዞራል
ግና በምላሹ ምስጢር መች ይነግራል
መስኮቴን ብከፍተው
በብርድ ልብሴ ላይ ኮከቦች ፈሰሱ
እውነትለፈለገ ውበት ነው ወይ መልሱ
                                    (በእውቀቱ ስዩም )

No comments:

Post a Comment