Saturday, March 23, 2013

ኢትዮጵያዊው የ2 ዓመት ከ7 ወር ህፃን በውሀ ዋና 50 ሜትር ደረት ቀዘፋ ከ3 ደቂቃ በታች አጠናቀቀ::

   
ኢትዮጵያዊው የሁለት ዓመት ከ7 ወር እድሜ ያለው ህፃን በውሀ ዋና 50 ሜትር ደረት ቀዘፋ ከ3 ደቂቃ በታች በመግባት አጠናቀቀ፡፡ ህፃን ዳግም ኪሮስ ይባላል፡፡ እድሜው 3 ዓመት አልሞላም ገና 2 ዓመት ከ7 ወሩ ነው ዋና መዋኘት የጀመረው ደግሞ ከተወለደ በ6ኛ ወሩ ላይ ነው ፡፡ ነፃ ቀዘፋ፣ ደረት ቀዘፋጀርባ ቀዘፋ እና ቢራቢሮ የተባሉትን አራቱን የዋና አይነቶች በሚገባ ይዋኛል፡፡
  በአገር አቀፍ የትምህርት ቤቶች ስፖርት ፌስቲቫል የውሀ ዋና ውድድር መጋቢት 12/2005 ዓ.ም ፍፃሜውን ሲያገኝ ህጻኑ 5 ሜትር ጥልቀት እና በጣም ቅዝቃዜ ባለው የግዮን ሆቴል መዋኛ ገንዳ 50 ሜትር ደረት ቀዘፋ በ2 ደቂቃ ከ42 ሴኮንድ በማጠናቀቅ ተመልካቹን አስደምሟል፡፡ የ50 ሜትር ደረት ቀዘፋ የኢትዮጵያ ክብረ ወሰን 34 ሴኮንድ ሲሆን በታላቅ ወንድሙ ሮቤል ኪሮስ እጅ ይገኛል፡፡ ለህጻን ዳግም ኪሮስ ዋና በማለማመድ ትልቅ ስራ የሰሩት የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት አባቱ አቶ ኪሮስ ሀብቴ ናቸው፡፡ልጃቸው በቅርብ አመት ጊዜ ውስጥ አስገራሚ ታሪክ ይሰራል ብለዋል፡፡ 5 ልጆች ያሏቸው አቶ ኪሮስ ሶሰት ልጆቻቸው በኢትዮጵያ ውሃ ዋና ብሄራዊ ቡድን ወስጥ ተወዳዳሪዎች ናቸው፡፡
    ሁለቱ በእንግሊዝ አገር በዋና ስልጠና ላይ ይገኛሉ፡፡የህጻኑ እናት ወይዘሮ አዜብ መስፍን እና ታላቅ ወንድሙ ሮቤል ኪሮስ ለወደፊት በኦሎምፒክ ወርቅ ያመጣል ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል፡፡ ልጆች በራሳቸው ፍላጎት ማደጋቸው ጠቃሚ መሆኑንም ገለጸዋል፡፡ህጻን ዳግም ኪሮስ በቀጣይ ወር አዳማ ላይ በሚካሄደው የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ሻምፒዮና ላይ ትርዒት በማሳየት ተሳታፊ ይሆናል ተብሏል፡፡

No comments:

Post a Comment